28/05/2026
እርግዝና እና የሆድ ድርቀት/ Constipation in Pregnancy
በእርግዝና ጊዜ የሆድ ድርቀትና ተያይዞየሚመጣ የሆድ መነፋት ስሜትበአንድ ወቅትወይም በሌላ ሊያጋጥም ይችላል።
ለዚህ 3 ዋናዋና መነሻምክንያቶችይጠቀሳሉ፡-
👉ሰውነትሽ ለወሊድ እንዲዘጋጅ የሚያደርገው “ፕሮጄስትሮን”ሆርሞን የአንጀትጡንቻ እንዲላላ ስለሚያደርግ ምግብቶሎ አይንሸራሸርም። ይህምግብውስጥያሉ ንጥረነገሮች በደንብ እንዲመጠጡእናለልጅሽ እንዲደርሱቢያስችልም፣ድርቀትሊያመጣ ይችላል።
👉የማሕጸን መጠን መጨመር አንጀት ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደ ወትሮው ሥራውን እንዳያከናውን እንቅፋት ይሆናል።
👉 በእርግዝና ጊዜ የሚወሰዱ ቫይታሚኖች ውስጥ የሚገኘውየብረት ማዕድን (አይረን) መብዛት (አስፈላጊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ)፣ የምግብ መፈጨትንበመቀነስ ድርቀት እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል።
ድርቀትን ለማስወገድ ላድርግ?
• “ፋይበር” ያላቸውንምግቦች በብዛት መመገብ በቀን ቢያንስ ከ25 እስከ 30 ግራም ፋይበር መመገብ ይመከራል። ፋይበር (ጭረት) በተክሎች ውስጥ የሚገኝና ጨጓራ ስለማይፈጨው ሆድ የሚያለሰልስ ነው፤ ፍራፍሬዎች፣ አትክልት (በጥሬው ወይም ሙክክ ብሎ ሳይበስል፣ ከተቻለ ሳይላጥ) የመሳሰሉት በፋይበር የበለጸጉ ናቸው።
• ውሃ በብዛት መጠጣት በቀን ከሚመከረው መደበኛ 6 ብርጭቆ ውሃ በላይ 8 ብርጭቆ (ከአንድ ተኩል እስከ 2 ሊትር) ውሃመጠጣት ድርቀትን ለመቀነስ ይረዳል።
• ተስማሚ የአካልብቃት እንቅስቃሴማድረግ አንዱ የድርቀት መነሻ ሰበብ ጽንሱ አንጀት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደመሆኑ፣ በእግር ከመንሸራሸር አንሥቶ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ምግብእንዲንሸራሸርናድርቀት እንዲቀንስያግዛል።
📌የስራ ሰዓት:- 24 በሰዓት 7 ቀናት እንገኛለን
🚨ለህክምና አገልግሎት ማማከር እገልግሎት ከፈለጉ በ
📞+251936659999 / +251911194824 ይደውሉ።
Telegram፦t.me/biruksewclinic
Facebook፦facebook.com/profile.php id=100063808903287
e-mail ፦[email protected]
Tiktok፦ user731617208715
Dylan Page - News Daddy Kana TV ゚viralシ