18/10/2026
የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ቀደም ሲል በኡጋንዳ እና በአሁኑ ወቅት በኬንያ መከሰቱን ተከትሎ፣ የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI)፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር በሽታው ወደ ሀገራችን እንዳይገባና ቢከሰትም በፍጥነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅነት ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በአየርና በየብስ መግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የጤና ቅኝትና ቁጥጥር እየተካሄደ ሲሆን፣ የላቦራቶሪ ምርመራ አቅምን የማጠናከር፣ የልየታ እና ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድኖችን የማደራጀት፣ የበሽታ ክትትልን የማጠናከርና ዝግጁ የማድረግ ሥራዎችም እየተከናወኑ ይገኛል፣ በሽታው ከተከሰተባቸው ሀገሮች ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ሰዎች 24/7 ቅኝት፣ ልየታ እና ክትትል እየተካሄደም ይገኛል።
ሕብረተሰባችንም እንደተለመደው በበሽታው ዙሪያ የሚሰጡ ይፋዊ መረጃዎችን እንዲከታተልና
• የበሽታው ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው ሀገራት የሚመጡ ወይም ለበሽታው ተጋላጭ ከነበሩ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ትኩሳት፣ የጡንቻ ሕመም፣ ማስታወክ ወይም ያልተለመደ የደም መፍሰስ ጨምሮ የበሽታው ምልክቶች ከታዩባቸው ወዲያውኑ ለጤና ባለሙያ/ጤና ተቋም በማሳወቅ ተገቢውን የጤና ምርመራና ክትትል ማድረግ፤
• የበሽታውን ምልክቶች የሚያሳይ ማንኛውም ሰው በሚመለከቱበት ጊዜ በአቅራቢያ በሚገኝ የጤና ተቋም ሪፖርት ማድረግ ወይም በ8335 እና 952 ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry ofበ Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V