Health and medicine

Health and medicine this page is to provide general knowledge about health,diseases,and treatment especially drug related

25/06/2026

“የግፊት መድሀኒት አልጀምርም ፤ በምግብ አስተካክለዋለሁ”

✅ እውነታ (Fact): ጤናማ አመጋገብ እና የአኗኗር ለውጦች የደም ግፊትን ለመቆጣጠር በጣም አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ለብዙ ሰዎች እነዚህ ብቻ በቂ አይሆኑም።

የደም ግፊቱ ከፍ ያለ ከሆነ ወይም ሌሎች እንደ ስኳር በሽታ፣ የኩላሊት ችግር እና የልብ በሽታዎች ካሉ፣ መድሀኒት መጀመር ሊያስፈልግ ይችላል።

ብዙ ሰዎች:
• "ጨው መተው ብቻ በቂ ነው"
• "ምልክት የለኝም፣ ስለዚህ መድሀኒት አያስፈልገኝም"
• "አንዴ ከጀመርኩት እድሜ ልኬን መውሰድ አለብኝ"
• "መድሀኒት ኩላሊቴን ይጎዳል"
ብለው ይፈራሉ። ይህ ግን ትክክል አይደለም።

⚠️ የደም ግፊት መድሀኒት የሚረዳው:
• የደም ግፊትን በትክክለኛው መጠን (range )ለማቆየት
• የአንጎል ደም መፍሰስን (stroke) ለመቀነስ
• የልብ ድካምን እና የልብ ህመምን ለመከላከል
• የኩላሊት ጉዳትን ለመቀነስ
• ለረጅም ጊዜ የልብና የደም ሥር ጤናን ለመጠበቅ
ነው።

❗ የደም ግፊት ብዙ ጊዜ (silent killer) ነው።
ብዙ ሰዎች ምንም ምልክት ሳይኖራቸው ለዓመታት ከፍተኛ የደም ግፊት ሊኖራቸው ይችላል። ስለዚህ "ምልክት የለኝም" ማለት የደም ግፊቱ ትክክለኛ መጠን(normal range) ነው ማለት አይደለም።

⚠️ የግፊት መድሀኒትን በሀኪም ምክር አለመጀመር ወይም ማቆም ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ጉዳቶች:

• የአንጎል ደም መፍሰስ (stroke)
• የልብ ድካም (heart failure)
• የልብ ህመም (heart attack)
• የኩላሊት ሥራ መቀነስ
• የዓይን ደም ሥሮች ጉዳት
• ድንገተኛ የግፊት መጨመር (hypertensive crisis)

❗ **አንዳንድ ሰዎች ጤናማ አኗኗር ከተከተሉ በኋላ የመድሀኒት መጠናቸው ሊቀንስ ወይም አንዳንድ መድሀኒቶች ሊቆሙ ይችላሉ። ይህ ግን በሀኪም ምክር ብቻ መደረግ አለበት።

✅ የደም ግፊት መድሀኒት ለመጉዳት ሳይሆን፣ ልብን፣ አንጎልን፣ ኩላሊትን እና የደም ሥሮችን ከከባድ ጉዳት ለመጠበቅ የሚረዳ ሕክምና ነው።

📚 References:
• 2024 ESC Guidelines for the Management of Elevated Blood Pressure and Hypertension.
• 2020 International Society of Hypertension Global Hypertension Practice Guidelines.
• 2017 ACC/AHA Guideline for the Prevention, Detection, Evaluation, and Management of High Blood Pressure in Adults.

"ታላቁ አስመሳይ" - ሲስተሚክ ሉፐስ ኤራይቲማቶሰስ (SLE)ሲስተሚክ ሉፐስ ኤራይቲማቶሰስ (SLE) የሰውነት በሽታ መከላከያ ሥርዓት ተሳስቶ የራሱን ጤናማ ሕዋሳት እና አካላት የሚያጠቃበት (...
15/06/2026

"ታላቁ አስመሳይ" - ሲስተሚክ ሉፐስ ኤራይቲማቶሰስ (SLE)

ሲስተሚክ ሉፐስ ኤራይቲማቶሰስ (SLE) የሰውነት በሽታ መከላከያ ሥርዓት ተሳስቶ የራሱን ጤናማ ሕዋሳት እና አካላት የሚያጠቃበት (Autoimmune) ሥር የሰደደ የሕመም ዓይነት ነው።

ሉፐስ "ታላቁ አስመሳይ" (The Great Imitator) በመባል ይታወቃል። ምክንያቱም ምልክቶቹ ከሌሎች በርካታ በሽታዎች ጋር ስለሚመሳሰሉና ከሰው ሰው ስለሚለያዩ በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

በሽታው በብዛት የሚያጠቃው የመውለጃ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሴቶችን ሲሆን፣ በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያለው ጥሬ ጥምርታ 9 ለ 1 (9:1) ነው።

በሽታው እንዴት ይከሰታል? (Pathophysiology)
እንደ Harrison’s ገለጻ፣ የሉፐስ መነሻ በውል ባይታወቅም በጄኔቲክስ፣ በአካባቢያዊ ሁኔታዎች (ለምሳሌ ለፀሐይ ብርሃን መጋለጥ) እና በሆርሞን ለውጦች ምክንያት እንደሚከሰት ይታመናል።

Autoantibodies: የሰውነት በሽታ መከላከያ ሥርዓት Antinuclear Antibodies (ANA) የተባሉ ፀረ-ሰውነቶችን ያመነጫል። እነዚህ ፀረ-ሰውነቶች በሴል ውስጥ የሚገኘውን ኒውክሊየስ በማጥቃት በሰውነት ውስጥ ከፍተኛ መቆጣትን (Inflammation) ያስከትላሉ።

የሉፐስ ዋና ዋና ምልክቶች
ሉፐስ ማንኛውንም የሰውነት ክፍል ሊነካ ይችላል። ዋና ዋናዎቹ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦

የቆዳ ምልክቶች (Cutaneous)
Malar Rash: በሁለቱም ጉንጮች እና በአፍንጫ ላይ የሚወጣ የቢራቢሮ ቅርጽ ያለው ቀይ ሽፍታ።

Photosensitivity: ለፀሐይ ብርሃን ሲጋለጡ የሚወጣ ሽፍታ ወይም የሕመም ስሜት መጨመር።

የመገጣጠሚያ ሕመም (Musculoskeletal):
ከ90% በላይ ታካሚዎች ላይ የሚታይ ሲሆን፣ በተለይ ጠዋት ጠዋት የመገጣጠሚያ መገተር እና ሕመም ይታያል። Kelley’s እንደሚገልጸው፣ ይህ ሕመም እንደ ሩማቶይድ አርትራይተስ አጥንትን አይበላሽም (Non-erosive)።

የኩላሊት መቆጣት (Lupus Nephritis):

በጣም አስፈሪው የሉፐስ ክፍል ሲሆን፣ ኩላሊት ሥራውን በአግባቡ እንዳይሠራ ያደርጋል። ምልክቱም የሽንት መልክ መቀየር፣ የሽንት መብዛት ወይም ማነስ እና የእግር እብጠት ናቸው።

የልብና የሳንባ ችግሮች:
በልብ እና በሳንባ ዙሪያ ባሉ ስስ ሽፋን (Membranes) ላይ ፈሳሽ መከማቸት ወይም መቆጣት (Pleuritis/Pericarditis)።

የደም ችግሮች:
የደም ማነስ (Anemia)፣ የነጭ ደም ሴሎች ማነስ (Leukopenia) ወይም ፕሌትሌት ማነስ (Thrombocytopenia)።

የምርመራ ዘዴዎች (2019 ACR/EULAR Criteria)
የዓለም አቀፍ የሩማቶሎጂ ማኅበራት (ACR እና EULAR) ባወጡት አዲስ መመሪያ መሠረት፣ አንድ ሰው ሉፐስ አለበት ለማለት የሚከተሉት ቅደም ተከተሎች መሟላት አለባቸው፦

ቅድመ ሁኔታ (Entry Criterion): የ ANA የደም ምርመራ ውጤት Positive መሆን አለበት። ይህ ውጤት ኔጋቲቭ ከሆነ ሰውየው ሉፐስ የመያዝ ዕድሉ በጣም አነስተኛ ነው።

የነጥብ አሰጣጥ: ANA ፖዘቲቭ ከሆነ በኋላ፣ ታካሚው ያላቸው ምልክቶች ነጥብ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ፦
ትኩሳት (2 ነጥብ)
የቢራቢሮ ሽፍታ (6 ነጥብ)
የመገጣጠሚያ ሕመም (6 ነጥብ)
በሽንት ውስጥ ፕሮቲን መገኘት (4-10 ነጥብ)
ውጤት: አጠቃላይ ድምር ነጥቡ 10 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ታካሚው SLE አለበት ተብሎ ይደመደማል።

የሕክምና አማራጮች
ሉፐስ ሙሉ በሙሉ ባይድንም፣ በመድኃኒቶች አማካኝነት ምልክቶቹን መቆጣጠር እና የሰውነት ክፍሎች እንዳይጎዱ ማድረግ ይቻላል።

26/05/2026

ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ

በአፍሪካ ስለተከሰተው ኢቦላ ቫይረስ በሽታ እና በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች

ግንቦት 17-2018 ዓ.ም



የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በግንቦት 09 ፣ 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ (DRC) እና በዩጋንዳ በቡንዲቡግዮ (Bundibugio) ቫይረስ ዝርያ የሚመጣ የኢቦላ ቫይረስ በሽታ መከሰቱን ያሳወቀ ሲሆን እስከ ትላንት ግንቦት 16፣ 2018 ድረስ በእነዚሁ ሀገራት በአጠቃላይ ከ101 በላይ የሚሆኑ በላቦራቶሪ የተረጋገጡ ታማሚዎች እና ከ900 በላይ ንክኪ ያላቸው ተጠርጣሪዎች የህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ከፍተኛ የስርጭት እና የሞት ምጣኔ ያለው በሽታ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው በንክኪ በቀላሉ ይተላለፋል።

እስከዛሬ ድረስ በሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም አይነት በኢቦላ ቫይረስ በሽታ የተጠረጠረ ወይም የታመመ ሰው አልተገኘም።

ምንም እንኳን በሽታው ከተገኘባቸው አገራት ጋር ቀጥተኛ የድንበር ግንኙነት ባይኖረንም የበሽታውን አደገኛነት በመገንዘብ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (Africa CDC) የወረርሽኙን መከሰት ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ፦

🔹በሁሉም አለም አቀፍ የየብስ መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች የልየታ እና የቅኝት ስራዎች በማጠናከር ፣

🔹በአለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች የተጠናከረ ክትትል በማድረግ ፣

🔹የጤና ተቋማት ዝግጁ በማድረግ እንዲሁም የላቦራቶሪ አቅምን በማሳደግ

🔹እንዲሁም አስፈላጊው የህክምና ግብአት አቅርቦት ላይ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

✍️ ጤና ሚኒስቴር

▬▬▬▬▬▬▬▬▬

"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"

"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"

25/05/2026

ስር የሰደደ ድካም ምንድን ነው?

ስር የሰደደ ድካም (chronic fatigue syndrome)
ከስድስት ወራት በላይ የሚቆይ የማያቋርጥ ከፍተኛ ድካም ሲሆን እረፍት በማደረግ የማይለቅ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን የሚረብሽ ነዉ።

⚕️መንስኤዎች

🔹የደም ማነስ
🔹ሃይፖታይሮዲዝም
🔹የስኳርና የልብ ህመም
🔹ድባቴና ጭንቀት
🔹የተመጣጠነ ምግብ እጥረት
🔹የቫይታሚኖች እጥረት
🔹ብዙ ሰዓት ተቀምጦ ማሳለፍ
🔹በቂ እንቅልፍ አለማግኘት
🔹በተለያዩ ቫይረሶች የሚመጡ ኢንፈክሽኖች
🔹የሆርሞን መዛባት
🔹የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት

☤ ምልክቶች

🔸ከ6 ወር በላይ የቆየ የማያቋርጥ ድካም
🔸ትኩረት ማጣት
🔸የመርሳት ችግር
🔸ራስ ምታት
🔸በእንቅልፍ የማይለቅ ድካም
🔸የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም
🔸የድምፅና ብርሃን ስሜታዊነት

🔬 ምርመራዎች

▫️የደም ምርመራ
▫️የታይሮይድ ተግባር ምርመራ
▫️የስነ-አዕምሮ ምርመራ
▫️የልብ ምርመራ

🥼 ሐኪም ጋር መቼ መሄድ ይገባል?

▪️ከ6ወር በላይ የቆየ ድካም ሲኖር
▪️በዕለት ተዕለት ህይወት ላይ ተፅዕኖ ሲኖር
▪️ምክንያቱ ያልታወቀ ክብደት መቀነስ ሲኖር
▪️ትኩሳትና ሌሎች የህመም ስሜቶች ሲኖሩ

🩺 ህክምናዎች

➪ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
➪ ቫይታሚኖችን መጠቀም
➪ የጭንቀት ህመምን መታከም
➪ የህመም ማስታገሻ መዉሰድ
➪ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
➪ ከመጠን በላይ የሆነ ጭንቀትን ማስወገድ
➪ በቂ ዉሃ መጠጣት
➪ ጤናማ እንቅልፍ ማግኘት
➪ አልኮልና አነቃቂ መጠጦችን ማቆም

 ((  ) የሲያቲካ ህመም(sciatica pain) በሲያቲክ ነርቭ (Sciatic Nerve) ላይ የሚከሰት ህመም ነው። ይህ ነርቭ ከበታች የጀርባ አንገት (Lower Back) ጀምሮ በእግር ው...
27/04/2026

(( )
የሲያቲካ ህመም(sciatica pain) በሲያቲክ ነርቭ (Sciatic Nerve) ላይ የሚከሰት ህመም ነው።
ይህ ነርቭ ከበታች የጀርባ አንገት (Lower Back) ጀምሮ በእግር ውስጥ እስከ ጣቶች ድረስ የሚዘረጋ ትልቅ ነርቭ ነው።

የሲያቲካ ህመም ብዙውን ጊዜ በአንድ ወገን (አንድ እግር) ላይ ይሰማል፣ እና ከቀላል እስከ ከባድ ህመም ሊሆን ይችላል።

#ምልክቶች
====
1. የጀርባ እና የዳሌ ህመም:
ህመሙ ከበታች የጀርባ አንገት ጀምሮ በእግር ውስጥ ወደ ታች ይዘረጋል።
ከዳሌ ጀምሮ ወደ ታች ወደ ጉልበት የሚነዝር ህመም የህመም ስሜት ይኖረዋል
2. በእግር ውስጥ ህመም: ብዙውን ጊዜ በአንድ እግር ውስጥ ይሰማል፣ እና ከጉልበት ጀምሮ እስከ ጣቶች ድረስ ሊዘረጋ ይችላል።

3.ንዝረት ወይም እብጠት: በእግር ውስጥ የሚሰማ የንዝረት ስሜት፣ አልፎ አልፎም የጫማ እብጠት ሊኖረው ይችላል ።
4. የእግር አጥብቆ አለመርገጥ(ደካማነት): በእግር ውስጥ የኃይል እጥረት ወይም አጥብቆ አለመርገጥ ሊያስከትል ይችላል።

5. የማቃጠል ስሜት: በእግር ውስጥ የሚሰማ ንዝረት (Tingling) ወይም የማቃጠል ስሜት (Burning Sensation)።

#ምክንያቶች
=====
1. የድስክ ስርዓት ችግር (Herniated Disc): በጀርባ ውስጥ ያሉ ድስኮች (Discs) ሲንሸራተቱ ወይም የመቆጣት ስሜት ሲኖራቸው ሲያቲክ ነርቭ ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ::

2. የአከርካሪ አጥንት ጥበት (Spinal Stenosis): ከቅንጭላት የሚመጡ ነርቮች የሚወጡበት የጀርባ አከርካሪ አጥንት ሲጠበብ ሲያቲክ ነርቭ ላይ ጫና ያሳድራል።

3. የጡንቻ መሸማቀቅ (Muscle Strain): በጀርባ ወይም በጉልበት ውስጥ ያሉ ጡንቻዎች ሲጎዱ ሲያቲክ ነርቭ ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ።

4. ሌሎች ምክንያቶች: እንደ የጀርባ አከርካሪ አጥንቶች አደጋ፣ የመቀመጫ አጥንት ችግሮች፣ አንዳንዴም በእርግዝና ወቅት በሚፈጠር የጀርባ አከርካሪ ጫና እንድሁም በመርፌ መድሀኒት ሲሰጡ በድንገት ነርቩ ከተወጋ።

#ህክምና
====
1.

- ህመም ማስታገሻዎች (Pain Relievers) መውሰድ ለምሳሌ አይቡፕሮፌን (Ibuprofen) ወይም ናፕሮክሰን (Naproxen)።
- የነርቭ ህመም ለማከም መድሃኒቶች (Gabapentin ወይም Pregabalin)።
- በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ የስቴሮይድ መድሃኒቶች (Steroids)።

2. ስራ (Physical Therapy):

- የጀርባ አንገት እና የጉልበት ጡንቻዎችን ለማጠናከር የሚያገለግሉ ልምምዶች።

3. #በከባድ ሁኔታዎች እንዳስፈላጊነቱ :
- ቀዶ ሕክምና (Surgery) ለምሳሌ :የድስክ መንሸራተት ሲኖር
:የጀርባ አከርካሪ አጥንቶች ጥበት ሲኖር

#መከላከል
===
1. ትክክለኛ የሰውነት አቀማመጥ (Posture): በተለይ በተቀመጥበት ወይም በቆመበት ጊዜ።

2. የአካል ብቃት ልምምድ: የጀርባ አንገት እና የጉልበት ጡንቻዎችን ማጠናከር።

3. ከባድ ነገሮችን ከመስራት መቆጠብ: በትክክል የማይሰሩ የአካል ብቃት ልምምዶችን ማስቀረት።

#ማስታወሻ

የሲያቲካ ህመም በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም፣ በአብዛኛው ጊዜ በትክክለኛ ሕክምና እና በአካል ብቃት ስራ ሊታከም ይችላል። ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ወደ የሕክምና ባለሙያ መሄድ አለባቸው።

🩺 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (UTI) እና በግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች (STIs) ልዩነቶች🩺👉ብዙ ሰዎች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን (UTI) እና በግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን (STIs...
23/04/2026

🩺 የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (UTI) እና በግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች (STIs) ልዩነቶች🩺

👉ብዙ ሰዎች የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን (UTI) እና በግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን (STIs) ያደባለቋቸዋል። ሁለቱም በሚሸኑበት ወቅት የማቃጠል ስሜትና ህመም ሊያስከትሉ ቢችሉም፣ መንስኤያቸውና ምልክቶቻቸው ግን ይለያያሉ።
📍 ዋና ዋና ልዩነቶች በንፅፅር
* መንስኤ፦
* UTI፦ በአብዛኛው የሚከሰተው ባክቴሪያዎች (በተለይ *E. coli*) ወደ ሽንት ቧንቧ ሲገቡ ነው። ከወሲባዊ ግንኙነት ውጭም ሊከሰት ይችላል።
* STIs፦ በወሲባዊ ግንኙነት አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው በሚተላለፉ ባክቴሪያዎች፣ ቫይረሶች ወይም ጥገኛ ተሕዋስያን የሚመጡ ናቸው።
* የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (UTI) ምልክቶች፦
* ቶሎ ቶሎ የመሽናት ፍላጎት (ምንም ሽንት ባይኖርም እንኳ)።
* ሲሸኑ የማቃጠል ስሜት።
* የሽንት መልክ መቀየር (መደብዘዝ) ወይም መጥፎ ሽታ ያለው ሽንት።
* በዳሌ አካባቢ የሚሰማ ህመም።
* በግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች (STIs) ምልክቶች፦
* ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ (ከሽንት ውጭ የሆነ)።
* በብልት አካባቢ የሚወጡ ቁስሎች፣ እብጠቶች ወይም ሽፍታዎች።
* ከፍተኛ የማሳከክ ስሜት።
📍 የሕክምና ልዩነት
* UTI፦ አብዛኛውን ጊዜ በአጭር ጊዜ የጸረ-ባክቴሪያ (Antibiotics) ሕክምና ይድናል።
* STIs፦ እንደ በሽታው ዓይነት ይለያያል፤ ባክቴሪያ ለሆኑት (እንደ ጨብጥና ክላሚዲያ) ጸረ-ባክቴሪያ፣ ለቫይረሶች (እንደ ሄርፒስ) ደግሞ ጸረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ይታዘዛሉ።
🚩 ሐኪም ማማከር ያለብዎት መቼ ነው?
በሚሸኑበት ወቅት ህመም ወይም ማቃጠል ካለዎት በአስቸኳይ ምርመራ ማድረግ ይኖርብዎታል። የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሳይታከም ከቆየ ወደ ኩላሊት ሊሰራጭ ይችላል፤ በግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ደግሞ ዘላቂ የሆነ የመካንነት ወይም ሌላ የጤና ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ቢረዝምም በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው ለሌሎች እንዲደርስ በማረግ ተባበሩየስኳር ህመም ምን ማለት ነው? • የስኳር ህመም በደም ውስጥ በሚፈጠር ክልክ ያለፈ የስኳር መጠን ሳቢያ  የሚከሰት የእድሜ ...
13/03/2026

ቢረዝምም በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው ለሌሎች እንዲደርስ በማረግ ተባበሩ
የስኳር ህመም ምን ማለት ነው?
• የስኳር ህመም በደም ውስጥ በሚፈጠር ክልክ ያለፈ የስኳር መጠን ሳቢያ የሚከሰት የእድሜ ልክ የጤና ችግር ነው፡፡
• ይህ ችግር የሚከሰተው ቆሽት የተባለው የሰውነታችን ክፍል የሚያመነጨው ኢንሱሊን እጅግ አነስተኛ ሲሆን ወይም ኢንሱሊን ማመንጨት ሲያቆም ነው።
• ኢንሱሊን በቆሽት ውስጥ የሚፈጠር ንጥረ ቅመም (ሆርሞን) ነው።
• የ ኢንሱሊን ዋና ስራ በደም ውስጥ የሚገኝ ስኳርን ኃይል ወደ ሚያስፈልጋቸው የተለያዩ
• የሰውነት አካሎች ያሰራጫል።
• በደማችን ውስጥ ያለው ስኳር የሚገኘው ከምንመገበው ምግብ ነው።
• የስኳር ህመምዎን በአግባቡ በመከታተል ጤናማ መሆን እና እንደማንኛውም ሰው በማንኛውም ስራ ላይ በመሰማራት አምራች ዜጋ መሆን ይችላል።
የስኳር ህመም ዓይነቶች
1ኛው ዓይነት የስኳር ህመም
• የዚህ ዓይነቱ የስኳር ሀመም የሚከሰተው ቆሽት ኢንሱሊን ማመንጨት ሲያቆም ነው። አብዛኛውን ጊዜ በሀፃናት ላይ እና ከ3ዐ ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ በድንገት ይከሰታል። በአሁኑ ጊዜ ባለው የህክምና እውቀት መሰረት ልንከላከለው አንችልም፡፡ ህመሙ በኢንሱሊን መታከም ይኖርበታል።
2ኛው ዓይነት የስኳር ህመም
• አካላችን የሚያመነጨውን ኢንሱሊን መጠቀም ሳይችል ሲቀር ወይም ሰውነታችን በቂ የሆነ ኢንሱሊን ማመንጨት ሲያቅተው የሚፈጠረው የስኳር ህመም ዓይነት ነው።
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግና ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ የእድሜ መግፋትና በቤተሰብ ውስጥ የስኳር ህመም መኖር ለሁለተኛው ዓይነት የስኳር ሀመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ናቸው።
• ሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም በመድኃኒት፣ ጤናማ አመጋገብ በመከተልና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማደረግ ይታከማል። በቁጥጥር ስር ያልዋለ የስኳር ህመም ሀልውናችንን አደጋ ላይ ሊጥሉ ለሚችሉ
o እንደ የግማሽ አካል መስነፍ (ስትሮክ)፣
o የልብ ድካም፣
o የኩላሊት ተግባሩን በትክክል መስራት አለመቻል፣
o የዓይን ብርሃን ማጣትና
o የእግር መቆረጥን ለመሳሰሉ ችግሮች ያጋልጠናል።
አንደኛው ዓይነት የስኳር ህመም
• በሚከሰትበት ጊዜ ቆሽት ኢንሱሊን አያመርትም። ስለዚህ ኢንሱሊን መውሰድ ያስፈልጋል። ሀዋሳቶቹን ለመክፈት ሁሉም የኢንሱሊን ቁልፎች የሚመጡት ከሰውነት ውጪ ነው።
ሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመም
• ሲከሰት ቆሽት የሚያመርተው ኢንሱሊን በቂ አይሆንም ህዋሳትም ኢንሱሊንን በደንብ አይቀበሉም። ስለዚህ በቂ ኢንሱሊን ለማግኘት ቆሽት ብዙ መስራት አለበት።
በደም ውስጥ የስኳር መጠን መብዛት
ምልክቶች
• ቶሎ ቶሎና በብዛት መሽናት
• የማያቋርጥ እና የማይረካ የውሃ ጥም ኃይለኛ የድካም ስሜት
• የሰውነት ክብደት መቀነስ
ሌሎች ምልክቶች
• ቁስሎች ቶሎ አይድኑም
• የማየት ችግር ይገጥምዎታል
• ሌሎች በሽታዎች (ለምሳሌ የሽንት ማስተላለፊያ ቱቦ ችግር)
• የቆዳ ማሳከክ
• እጅ እና እግር መደንዘዝ
በቁጥጥር ስር ያልዋለ የ ስኳር ህመም የሚያስከትላቸው ረጅም ጊዜ ጠንቆች
• ስትሮክ (ግማሽ ሰውነት መስነፍ)፥
• የአይን ብረሃን ማጣት፥
• የልብ ድካም፥
• የኩላሊት መድከም፥
• ስንፈተ ወሲብ፥
• የነርቭ ችግር፥
• የእግር ቁስለት
ከስኳር ህመም ጋር የሚኖር ሰው ምን ማድረግ ይገባዋል?
ጤናማ አመጋገብ
• በየእለቱ በተመሳሳይና መደበኛ በሆኑ ሰዓታት አነስተኛ ምግቦችን መመገብ።
• በእያንዳንዱ የምግብ ክፍለ ጊዜ ሐይል ሰጪ ምግብ ማካተት
• ቅጠላ ቅጠል በብዛት መመገብና
• ፍራፍሬዎችንም ጨምሮ መመገብ
• ቅባትና ጨው የበዛባቸውን እንዲሁም ጠፋጭ ምግቦችን መቀነስ
የሰውነት እንቅስቃሴ
• በየእለቱ ፈጠን ባለ እርምጃ ቢያንስ የ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ
ለእግር ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ
• በየእለቱ የእግርን ዙሪያ-ገባውን ማየትና የደረሱ ጉዳቶች ካሉ መስታዎት በጠቀም ማስተዋል
• በባዶ እግርዎ አይጓዙ
• እግርዎን ከታጠቡ በኋላ በጣቶች መሀል ጨምር በማድረቅ ቅባት መቀባት
• ሲጋራ ፈጽሞ አለማጨስ
ክብደትን መከታተል
• የሰውነት ክብደትን ለመከታተል መዝግቦ ማስቀመጥ
• የሰውነት ክብደት ያለማቋረጥ የሚቀንስ ከሆነ ሀኪም ዘንድ መሄድ
• የእፍንና የጥርስን ጤንነት መጠበቅ
• ከምግብ በኋላ አፍን መጉመጥመጥ እንደዚሁም ጥርስን በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ማጽዳት፣
• የሚደሙ ድዶች/በአፍ አካባቢ የማይድኑ ቁስሎች ካሉ ሀኪም ዘንድ መሄድ
በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን መረዳት
• በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በየጊዜው መከታተል፣ አልያም በላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ በተጨማሪም ላቦራቶሪ
• በመሄድ ኤችቢኤዋንሲ/HBA1C) ማለትም በ አማካይ የሶስት ወራት የስኳር ውጤት ምርመራ ማድረግ
• ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የዓይን፣ የኩላሊት፣ የነርቭ፣ የልብ፣ የደም ቅባት (ኮሌስትሮል) ምርመራ እንደአስፈላጊነቱ ሀኪምዎት በሚያዘው መሰረት ማድረግ ለ አይነት ሁለት (TYPE 2 DM) ከተገኘበት አመት ጀምሮ ለ አይነት አንድ ከሆነ (TYPE 1 DM) ከተገኘ ከአምስት አመት በኋላ ወይም ህፃናትከሆኑ ዕድሜአቸው ከአስር ዓመት ሲያልፍ
• ኪኒኖችንም ሆነ ኢንሱሊንን ሀኪም ባዘዘው መሰረት መውሰድ ሀኪምዎን/ነርስዎን መደበኛ በሆነ ሁኔታ መጎብኘት ቢያንስ በዓመት 3-4 ጊዜ ሀኪም ዘንድ በመሄድ ምርመራ ማካሄድ።
ተገቢ በሆነ መንገድ ለእግረዎ እንዴት ጥንቃቄ ማድረግ ይችላሉ
• የሚመቹ ጫማዎችን ያድረጉ ለምሳሌ በጣም ያልጠበቁ እና ለእግረ ምቾት ያላቸው
• ሂል ያላቸውን (ከተረከዝ ከፍ ኣሉ) ጫማዎች አለመጠቀም
ተገቢ በሆነ መንገድ ለእግርዎ እንዴት ጥንቃቄ ማድረግ ይችላሉ?
የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ማስተዋል
• በእግር አሊያም ደግሞ በቁርጭምጭሚት ላይ መቅላትና ማበጥ
• እግር ይነፋፋል አሊያም ደግሞ ይቀጭጫል
• እግር እጅግ ይቀዘቅዛል
• በእግር ጉዞ ጊዜ አሊያም አረፍ ሲባል ሀመም ይሰማል
• የሚታዩ ክፍት ቁስሎች
• የማይድኑ ቁስሎች መኖር
• እግር ውስጥ የሚያድጉ የእግር ጥፍሮች
• እጅግ አነስተኛ ቁስል ብትሆን እራስዎ ለማከም አይሞክሩ።
• ሀኪምዎ/ነርስዎ ዘንድ ይሂድ።
• የስኳር ህመም እንክብሎችን መውሰድ
የስኳር ሀመም እንክብሎች ለምን ያስፈልጋሉ?
• ሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመምተኛ ከሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ በደምዎ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቀነስ ይችላሉ።
• መድሃኒትዎን መውሰድ ከረሱ በስኳር ህመም የተነሳ የሚመጡ የዓይንና የእግር ሀመምን የመሳሰሉ ውስብስብ ችግሮች ይገጥምዎታል።
• አንደኛው ዓይነት የስኳር ህመም በኪኒኖች አይታከምም። ስለዚህ ኢንሱሊን ብቻ በመርፌ መውሰድ ይኖርብዎታል።
• በደምዎ ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ይቀያየራል።
• በደም ውስጥ ከፍተኛ የስኳር መጠን አለ የሚባለው 200 ሚ.ግ/ ዴሲ ሊትር እና ከዛ በላይ ከሆነ
• ጤናማ የሚባለው 140 ሚ.ግ/ ዴሲ ሊትር (ከምግብከ ሁለት ሰዓት ቆይታ በኋላ 100 ሚግ/ ዴሲ ሊትር
• ከ 70 ሚግ/ ዴሲ ሊትር በታች ከሆነ አነስተኛ የስኳር መጠን ይባላል
የስኳር ህመም እንክብሎችን መውሰድ
የስኳር ሀመም እንክብሎች ለምን ያስፈልጋሉ?
• ሁለተኛው ዓይነት የስኳር ህመምተኛ ከሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ በደምዎ ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቀነስ
• ይችላሉ።
• መድሃኒትዎን መውሰድ ከረሱ በስኳር ህመም የተነሳ የሚመጡ የዓይንና የእግር ሀመምን የመሳሰሉ ውስብስብ ችግሮች ይገጥምዎታል።
• አንደኛው ዓይነት የስኳር ህመም በኪኒኖች አይታከምም ስለዚህ ኢንሱሊን ብቻ በመርፌ መውሰድ ይኖርቦታል
ጤናማ ምግብ ለመመገብ
• ሰውነትዎ ከሚፈልገው መጠን በላይ አይመገቡ። ክብደት እየጨመሩ ከሆነ ከመጠንዎ በላይ እየበሉ መሆኑን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።
• በእያንዳንዱ የምግብ ክፍለጊዜ አንድ ሀይል ሰጪ ምግብ ይመገቡ። በደም ውስጥ የሚገኘውን ስኳር ቀስ ብለው የሚጨምሩ እንደ እንጀራ፣ ድንች፣ ዳቦ እና አሰር የበዛባቸውን ምግቦች ይምረጡ።
• በእያንዳንዱ የምግብ ክፍለጊዜ የሚበሉትን የሀይል ሰጪ ምግብ መጠን ይገንዘቡ። ለምሳሌ ሁለት ቁርጥ እንጀራ፣ ሶስት ድንች የመሳሰሉት፣ ቤተሰቡ በሚመጉብበት ጊዜ የራስዎን የገበታ ዘዴ ቢከተሉ ይሀንን በተሻለ ሊገነዘቡ ይችላሉ።
• ፖስታ፤ ሩዝ፣ መኮሮኒ ከአትክልት ጋር በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ ቢመገቡ ስኳር ቶሎ እንዳይጨምር ይረዳል።
• ቅጠላቅጠል በብዛት ይመገቡ። ቅጠላቅጠሎችና ፍራፍሬዎች ሰውነትዎን ከበሽታ ይከላከላሉ። ከሀይል ሰጪ ምግቦችና ከስጋ በበለጠ በቀን ሁለት ጊዜ ቅጠላቅጠል ይመገብ።
• የሚመገቡትን የቅባት መጠን ይቀንሱ። ያልረጉ ቅባቶችን ለምሳሌ የሱፍ ዘይት እና የወይራ ዘይት የመሳሰሉትን ይጠቀሙ። ቅቤና ክሬሞችን ጭራሽ አይጠቀሙ /እጅግ ይቀንሱ።
• እንደ ከረሜላ፣ ኩኪስ የታሸጉ ጣፋጭ ምግቦች ኬኮች፣ ለስላሳ መጠጦች የመሰሰሉትን አይጠቀሙ።
• የአልኮል መጠጦችን ይቀንሱ
• ሲጋራ ፈጽሞ አያጨሱ
የገበታ ዘዴ
• የሚበሉትን ምግብ መለካት ሳያስፈልግዎ ጤናማ አመጋገብ የሚከተሉበት ዘዴ ነው።
• 20 ሴንቲሜትር የሚሆን ሳሀንዎን በቀን ውስጥ በሚያስፈልግዎ ቅጠላቅጠል፤ ሀይል ሰጪ ምግቦች እንዲሁም ስጋ ይሙሉ። ከዚያም በመቀጠል እንድ ፍራፍሬ አሊያ ደግሞ ከቅበት ነጻ የሆነ ወተት ያክሉበት።
• ቁርስ 50% ሃይል ሰጪ 25%ፕሮቲን (ስጋ) 25% ቅጠላ ቅጠል ከቅባት ነጻ የሆነ ወተት ያክሉበት።
ምሳ እና እራት
• 50% ቅጠላቅጠል 25%ፕሮቲን (ስጋ) 25 % ሃይል ሰጪ ፍራፍሬ ያክሉብት
• ሀይል ሰጪ የምንላቸው ምግቦች እንጀራ፥ ዳቦ፥ ድንች፥ መኮረኒ፥ ፓስታ፥ በቆሎ
• ቅጠላ ቅጠል የምንላቸው ምግቦች ሰላጣ፥ቆስጣ፥ቲማቲም፥ጥቅልጎመን፥ጎመን እና የመሳሰሉት
• ፍራፍሬ የምንላቸው ምግቦች ብርቱካን፥ ሙዝ፥ፓፓያ፥ማንጎ፥አፕል( እነዚህን ሳይበዛ ጠቀም ይመከራል)
• ፕሮቲን የምንላቸው ምግቦች ስጋ፥እንቁላል፥አሳ፥አኩሪአተር
• አዘውትረው መወሰድ የሌለባቸው ምግቦች ስኳር፥ኬክ፥ብስኩት፥የካርቶን ጁስ፥ኩኪሶች፥ኬኮች፥ለስላሳዎች፥ ከረሜላዎች፥እና ቅባት በዛባቸውመ ምግቦች
ሰውነታችን ኢንሱሊን የሚያመርተው ለምንድነው?
• ሰውነታችን ከበላነው ምግብ የሚገኘውን ስኳር በማቃጠል ኃይልን/ ጉልበትን ይፈጥራል።
• ቆሽት ኢንሱሊን ያመርታል። ኢንሱሊን የሕዋሳት በር ተከፍቶ ምግብ እንዲቀበሉ የሚያደርግ ንጥረ-ቅመም ነው።
በኢንሱሊን አቀማመጥ ላይ ልብ ሊሏቸው የሚገብ ጉዳዮች
• በተቻለ መጠን / ኢንሱሊንዎን የቅዝቃዜ መጠኑ ከ2-8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ ፍሪጅ ውስጥ ያስቀምጡ። ነገር ግን ኢንሱሊን እጅግ ቀዝቅዞ በረዶ መሆን የለበትም።
ሌሎች ኢንሱሊን የማስቀመጫ ዘዴዎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡-
• ውሃ በማያስገባ እንደ ውሃ ፕላስቲክ በመሰለ እቃ ኢንሱሊንን በማኖርግማሽ ውሃ የተሞላበት የሽክላ እንስራ ውስጥ ማስቀመጥ ይችላል።በቤት አካባቢ ጉድጎድ ቆፍሮ አሸዋ በመሙላት ኢንሱሊንን በፕላስቲክእቃ በማኖር እዚያ ውስጥ ማስቀመጥ ይቻላል። አሸዋውን ግን እርጥበት እንዲያገኘው ማድረግ ተገቢ ነው።
• ኢንሱሊንን በጨርቅ ጠቅልሎ ማስቀመጥና ጨርቁን እርጥበት እንዲያገኝ ማድረግ።
• ኢንሱሊንን ሀጻናት በማይደርሱበት ቦታ ማስቀመጥ የግድ ነው።
• ኢንሱሊን የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው ቦታ መቀመጥ አለበት። ሞቃታማ ቦታ መቀመጥ የለበትም።
• የኢንሱሊን መርፌ በንፁህ ሳጥን ውስጥ በንፁህ አካባቢ መቀመጥ አለባቸው፡ ስሪንጅ ሲጠቀሙ ክዳኖቹን በንፁህ ሳጥን ውስጥ ያስቀምጡ።
• ፈፅሞ መርፌ እና ሌላ ሰው የተጠቀመውን የኢንሱሊን ብልቃጥ ከሌላ ሰው ጋር አይጋሩ። ለተለያዪ ኢንፌክሽኖች ያጋልጥዎታል።
ኢንሲሊንን ስለመውጋት
• መርፌዎን በጥንቃቄ ይጠብቁ።
• ፈፁሞ መርፌዎን ከማንም ጋር አይጋሩ። ለኢንፌክሽን ያጋልጥዎታል።
• በብልቃጡ ውስጥ ያለውን ኢንሱሊን ለማዋሃድ በመዳፍዎ ቀስ እያሉ 20 ጊዜ ለሁለት ደቂቃ ማሽከርከር፣ ፈፅሞ ግን አይነቅንቁ።
• መርፌው የሚገባበትን የሰውነት አካል ማፅዳት፣ ከመውጋት በፊት እርጥበቱ እንዲደርቅ ማድረግ ፈፅሞ መርፌዎን በአልኮል አለመጥረግ
• በሚወጉበት ጊዜ ቆዳን ቆንጥጦ ከፍ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ኢንሱሊኑ ሰውነት ውስጥ ገብቶ እስኪያልቅ መርፌውን ከመንቀልዎ በፊት ከ1-10 ይቁጠሩ (10 ሰኮንድ)
ኢንሱሊን የሚወጋበት ቦታዎች
• ክብደቱ ከፍ ያለ ሰው መርፌ ሲወጋ በ90 ዲግሪ አንግል ቀጥ አድርጎ ሊውጋ ሲገባ፣ ቀጠን ያለ እካል ያለው ደግሞ በ45 ዲግሪ በማንጋለል ሊወጋ ይገባዋል።
ልብ ሊሉት የሚገባ፡
በየጊዜው በሚወጉበትን ቦታ ይቀያይሩ። ሆድ ላይ ሲወጉ ከእምብርትዎ ሁለት ጣት ርቀት ይወጉ።
በደም ውስጥ አነስተኛ የስኳር መጠን ሲኖር የሚታዩ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችና ህክምናቸው።
• መጀመሪያ የሚታዩ ምልክቶች (ማላብ፥ማንቀጥቀጥ፥ፍጥነት ያለው የልብ ምት፥ማቅለሽለሽ፥ እራስ ምታት፥ ግራ መጋባት)
• ቀጥሎ የሚታዩ ምልክቶች፡(ረሃብ፥ መረበሽ፥ ድካምና የማስተዋል ችግር)
• አደገኛ ምልክት፡.(ራስን መሳት) በአስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት ይገባዎታል።
ምን መደረግ አለበት?
በአስቸኳይ ስኳር ያላቸውን ምግቦች መብላትና መጠጣት
• ጥቂት ከረሜላዎች
• አንድ ብርጭቆ የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ለስላሳ
• አራት የሻይ ማንኪያ ስኳር በማድረግ አንድ ብርጭቆ ሻይ መጠጣት።አንድ የሻይ ማንኪያ ማር መውሰድ
በደም ውስጥ የሚኖረው የስኳር መጠን መቀነስ
• በደም ውስጥ የሚኖረው የስኳር መጠን መቀነስ የምንለው ከ70 ሚግ በዴሲ ሊትር በታች ሲሆን ነው።
ምክንያቶች፡
• የምግብ ሰዓትን ማዘግየት ፥ ጥቂት ምግብ መመገብ/ በተለይ ኃይል ሰጪ፥ ምግብ ሳይበሉ አልኮል መውሰድ፥ አዘውትሮ የማይደረግ ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፥ ብዙ ኢንሱሊን/ኪኒን/ መውሰድ
በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለ መቀነስ እና ለመቆጣጠር፡
• የሚወስዱትን ኢንሱሊን/ክኒን መጠን ትክክለኛነት አረጋግጠው ይውሰዱ
• ምግብዎን ሰዓት ሳያሳልፉ ይመገቡ
• ኢንሱሊን በሚወጉበትና ምግብ በሚበሉበት ጊዜ መካከል ያለው ርቀት ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ
• የአካል ብቃት እንቅሳቃሴ ለማድረግ ካሰቡ የሚወስዱትን ኢንሱሊን መጠን ሀኪምዎ በሚነግርዎ መሰረት ይቀንሱ፤ ወይም አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ መክሰስ ይብሉ።

ኬቶጀኒክ ምግቦች• ኬቶጀኒክ ዳይት የምንላቸው ምግቦች በዋናነት o 70-80 % የፋት መጠንo 15-20% ፕሮቲን • 5-10% ካርቦሃይድሬት የያዙ የምግብ አይነቶችን ነው• በቀን  ውስጥ ምንጠ...
17/02/2026

ኬቶጀኒክ ምግቦች
• ኬቶጀኒክ ዳይት የምንላቸው ምግቦች በዋናነት
o 70-80 % የፋት መጠን
o 15-20% ፕሮቲን
• 5-10% ካርቦሃይድሬት የያዙ የምግብ አይነቶችን ነው
• በቀን ውስጥ ምንጠቀመው ካርቦሃይድሬት መጠን ከ 20 እስከ 50 ግራም ባለው ውስጥ ከሆነ ይሄም በ ክቶጀኒክ ዳይት ውስጥ ይካተታል
ጥቅማቸውስ
• ሰውነታችን እንደመጀመሪያ የሃይል ምንጭ ካርቦሃይድሬትን ይጠቀማል ነገር ግን ካረቦሃይድሬት መጠን ሲቀንስ ጉበት በሰውነታችን የሚገኘውን ስብ ወደ ኬቶን ቦዲ ((𝛽-hydroxybutyrate) በመቀየር ፋት እንደ ቀዳሚ የ ሃይል ምንጭነት ያገለግላል ያ ማለት ሰውነታችን እነዚህን Ketogenic ምግቦች እንደ ሃይል ምንጭነት መጠቀም ይጀምራል በዚህም የሚያስፈልገን የ ካርቦሃይድሬትን መጠን ይቀንሳል
• የ ካርቦሃይድሬትን አጠቃቀማችን ሲቀንስ በሰውነታችን የሚመረተው የ ኢንሱሊን መጠን ይቀንሳል
o የ ኢንሱሊን ቀዳሚ ስራ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ካርቦሃይድሬት ወይም ግልኮስ ሴሎች ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ በማድረግ ካርቦሃይድሬት እንደ የሃይል ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያደርጋል
• ከፍተኛ የ ካርቦሃይድሬት መጠን በሰውነት ውስጥ ካለ ሰውነታችን ከፍተኛ የሆነ ኢንሱሊን መጠን እንዲያመርት ይገደዳል ይሄን ደሞ ማድረግ የማይችሉት የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ናቸው ስለዚህ እነዚህ ክቶጀኒክ ምግቦች ዝቅተኛ የሆነ ካርቦሃይድሬት መጠን ስለያዙ የስኳር ታማሚዎች ከመድሃኒት ጎን ለጎን ቢጠቀሟቸው የራሳቸው ጥቅም እኖራቸዋል ማለት ነው
• በተጨማሪም ፋት ወደ ሃይል ምንጭነት ተቀየረ ማለት በሰውነታችን የሚገኝ የ ፋት መጠን ይቀንሳል በዚህም የሰውነት ክብደት መቀነስ ላይ የራሳቸው አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ማለት ነው
• አሁን ላይ እየወጡ ያሉ ጥናቶች የሚያሳዩት በመድሃኒት ብቻ መቆጣጠር ላልተቻለ የሚጥል በሽታ ላለባቸው በተለይ ህፃናት ላይ እስከ 50% ድረስ የሚጥል በሽታን የመቀነስ ጥቅም እንዳላቸው በጥናቶች ተረጋግጧል።
ምን አይነት መግቦች ይካተታሉ
• አሳ ፥ እንቁላል፥ አይብ፥ ስጋ፥ አቩካዶ፥ ለውዝ እና ጥራጥሬ ምግቦች ማንሳት ይቻላል
የሚያስከትሉት ችግር
• ሌላው እነዚህ ምግቦች በዋናነት በተጀመሩ የመጀመሪያ ሳምንት ላይ ማቅለሽለሽ ፥ ማዞር፥ እራስ ምታት የጡንቻ ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ
• ለረጅም ጊዜ እነዚህን ምግቦች የምንጠቀም ከሆነ
o የኩላሊት ጠጠር
o የአጥንት መሳሳት
o የ ዩሪክ አሲድ መጠን በሰውነት ውስጥ ስለሚጨምሩ የመገጣጠሚያ ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ
o ኬቶ ምግቦች ዝቅተኛ የሆነ ፋይበር መጠን ስላላቸው የሆድ ድርቀት ሊያስከትሉ ይችላሉ ፋይበር በሰውነታችን መፈጨት አይችልም በዚህም የሰገራ መጠን እንዲጨምር በማድረግ ፐሪስታለሲስ የአንጀት ጡንቻ መኮማተር እና መላለት እነዲኖር በማድረግ ሰገራ በቶሎ ከሰውነት እንዲወገድ ያደርጋል ፋይበር ደግሞ በብዛት የሚገኘው ከፍተኛ የካረቦሃይድሬት ምግቦች ላይ ነው
• እነዚህ ምግቦች ዝቅተኛ የሆነ የ ካርቦሃይድሬት መጠን ስለያዙ አብዛኛውን ፍራፍሬ እና አትክልቶችን መጠቀም አንችልም በዚህም የምናጣው የሚኒራል እና ቪታሚን እንደ vit A, E AND B6 FOLATE CALCIUM MAGNESIUM AND POTASSSIUM ያሉ ንጥረ ነገሮች በበቂ እንዳናገኝ ይሆናል
• እነዚህ ምግቦች ከፍተኛ የሆነ የፋት መጠን ስለያዙ የልብ ችግር ሊያስከትሉ ይችልላሉ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health and medicine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share