Benishangul Gumuz Health Bureau

Benishangul Gumuz Health Bureau ጤንነቱ የተጠበቀ ዜጋ እናፍራ
(1)

የክልሉን የላብራቶሪ ጥራት ለማሻሻያ  የዉጫዊ ጥራት ቁጥጥር /EQA / ሥራ ማጠናከር ወሳኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል መንግስት  ጤና ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ጤና ቢሮ እና ክልላዊ ላብራቶሪ ከአ...
04/06/2026

የክልሉን የላብራቶሪ ጥራት ለማሻሻያ የዉጫዊ ጥራት ቁጥጥር /EQA / ሥራ ማጠናከር ወሳኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ጤና ቢሮ እና ክልላዊ ላብራቶሪ ከአሶሳ ጤና ጣቢያ ጋር በዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር/EQA/ የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ
የክልሉን የላብራቶሪ ጥራት ለማሻሻያ የዉጫዊ ጥራት ቁጥጥር /EQA / ሥራ ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ነው ።

በየተቋማቱ የሚሰጠዉን የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ህሙማን ትክክለኛ የሆነ መድሀኒት እንዲያገኙ የሚያደርግ ስለሆነ የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደአለበት አቶ አለም ተናግረዋል ።

ቀደም ሲል በሁለቱ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ተገድቦ የነበረዉ የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ ወደ አሶሳ ጤና ጣቢያ መዉረዱ ማህበረሰቡ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ምክትል የቢሮ ሀላፊው አስገንዝበዋል ።

ምክትል የቢሮ ሀላፊው አክለውም የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ ይበልጥ ለማጠናከር የናሙና ቅብብሎሽ ሰንሰለት ማጠናከር ሲቻል በመሆኑ የናሙና ቅብብሎሽ ሰንሰለት ለማጠናከር የጤና ተቋማት በትኩረት መስራት እንደአለባቸዉ አሳስበዋል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ የጤና ተቋማት በላብራቶሪ አገልግሎት ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማወቅና የሚሰጠው የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።

ክልላዊ ላብራቶሪ ቀደም ሲል በወባ፣በቲቢ እና በኤች.አይ.ቨ ኤድስ በሽታዎች በመንግስትና በግል የጤና ተቋማት ላይ የዉጫዊ የጥራት ቁጥጥር /EQA/ ሥራ እንደሚሰራ ከመድረኩ ለማወቅ ተችሏል ።

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን!
04/06/2026

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁሉም አከባቢዎች በአይነት አንድ ክትባት እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን የፖሊዮ ቫይረስ (cVDPV1) ለመከላከል ሁለተኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከሰኔ 12-15/...
04/06/2026

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁሉም አከባቢዎች በአይነት አንድ ክትባት እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን የፖሊዮ ቫይረስ (cVDPV1) ለመከላከል ሁለተኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከሰኔ 12-15/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

ስለሆነም በተዋረድ የሚገኙ ወረዳዎችና ጤና ተቋማት በሙሉ ይህንን አውቃችሁ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንድታከናውኑ ቢሮው ያሳስባል።

ቀደም ሲል አንደኛ ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች ከሚያዝያ 30 /2018 ዓም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል።

የክልሉ ጤና ቢሮ!

የቤተሰብ  ዕቅድ  አገልግሎት ለማሻሻል  የሚመለከታቸው አካላት አቅም መገንባት  ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ።ቢሮው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአሶሳ ዞን 15 ጤና ኬላዎች ለተወጣጡ  የጤና  ...
03/06/2026

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ለማሻሻል የሚመለከታቸው አካላት አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ።ቢሮው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአሶሳ ዞን 15 ጤና ኬላዎች ለተወጣጡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በIUCD በቤተሰብ ዕቅድ ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ለማሻሻል በክልሉ ዘርፌ ብዙጨተግባራት እየተከናወኑ ቢሆንም የIUCD/ሉፕ/ አገልግሎት ሲታይ በጣም አነስተኛ ነው ።

ይህን አገልግሎት ለማሻሻልና አገልግሎቱን ወደ ተጠቃሚዎች ለማድረስ አገልግሎቱን የሚሰጡ ባለሙያዎችን በዘርፉ ማሰልጠን አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው እንዲሰጥ መደረጉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር ገልጸዋል ።

የክልሉን የቤተሰብ ጤና አገልግሎት በተለይም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያለዉን የIUCD/ሉፕ/ አገልግሎት ለማሻሻል በዘርፉ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ማሰልጠን እና እስከ አሁን በሆስፒታሎችና በጤና ጣቢያዎች ወደ ጤና ኬላዎች አገልገሎቱን ማዉረድ መሆኑን ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል ።

ምክትል ሀላፊዉ አክለውም ሰልጣኞቹ ስልጠናው በሚገባ ተከታትለው ወደ ተቋማቸው ስመለሱ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

በጤና ሚኒስቴር የወጣቶች፣አፍላ ወጣቶች እና የቤተሰብ ዕቅድ ዴስክ የቴክኒካል አማካሪ አቶ አስራት ሰበታ በበኩላቸው እንደሀገር የIUCE/ሉፕ / አጠቃቀም ሽፋን በተፈለገው መልኩ ባለመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠዉ በተቀመጠ ሀገራዊ ኢንሼቲቭ መሠረት አገልግሎቱን ለሚሰጡ ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጥ መደረጉን ተናግረዋል ።

IUCE/ሉፕ የቤተሰብ ዕቅድ ከጤና አንፃር ተስማም፣አንዴ ከተቀመጠ እስከ አስራ ሁለት አመት የሚያገለግል እና በጣም ርካሽ በመሆኑ እጅግ ተመራጭ የቤተሰብ ዕቅድ በመሆኑ ተመራጭ ነው ብለዋል።

ስልጠናው ከአሶሳ ዞን ከ8 የጤና ኬላዎች ለተወጣጡ 15 የጤና ኤክሰቴንሽን ባለሙያዎች ለተከታታይ 11 ቀን እንደሚሰጥ ከመረሀ ግብሩ ለማወቅ ተችሏል ።

Website :
http://www.bghb.gov.et
Facebook:-- https://www.facebook.com/share/1H9RGxJafc/
Telegram :-- https://t.me/bghealthbureauofficial
Twitter:- http://twitter.com/bghealth_bureau
YouTube :- http://www.youtube.com/

የአንድ ጤና/one health/ ፕሮግራም  ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተገለፀ ። ከአቡራሃሞ እና ከኡራ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ከተወጣጡ  የቴክኒክና የስትሪን...
30/05/2026

የአንድ ጤና/one health/ ፕሮግራም ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተገለፀ ። ከአቡራሃሞ እና ከኡራ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች ከተወጣጡ የቴክኒክና የስትሪንግ ኮሚቴ ጋር በአንድ ጤና ፕሮግራም አተገባበር ላይ ያተኮረ ዉይይት በአሶሳ ከተማ ተካሄዷል ።

የአንድ ጤና ፕሮግራም የሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶችን ባካተተ መልኩ የጋራ የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ወደ ሥራ ከገባ አመታትን ከአምስት አመት በላይ እያስቆጠረ ቢሆንም በተፈለገው መልኩ ወደ ሥራ በመግባት ዉጤት እያስመዘገበ አይደለም ።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ፕሮግራሙን ወደ ሥራ ለማስገባት የንቅናቄ መድረክ መዘጋጀቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና ምላሽ አሰጣጥ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰኚ መኮነን ገልጸዋል ።

የአንድ ጤና ፕሮግራም በሴክተሮች መካከል ያለዉን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የጎላ ድርሻ ስለአለው የሚመለከታቸው ሴክተሮች ለፕሮግራሙ ትኩረት መስጠት እንደአለባቸዉ አቶ ሰኚ ተናግሯል ።

አቶ ሰኚ አክለውም አሁን በዓለም ላይ ካለዉ የአየር ንብረት ለዉጥ፣የአመጋገብ ሥርዓት መቀየር፣ግሎባላይዜሽን ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ለመከላከል የአንድ ጤና/one health/ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ አማራጭ የለለው ተግባር መሆኑን አስረድተዋል ።

በማነቃቀያ መድረኩ ላይ ከአንድ ጤና በተጨማሪ በወቅታዊ የኢቦላ በሽታ ነባራዊ ሁኔታና የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት በመጡ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራም ተሰርቷል

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው አንድ ጤና/one health/ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር በተጨማሪ በሴክተሮች መካከል ያለዉን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር የጎላ ድርሻ እንዳለው ተናግረው ለተግባራዊነቱ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

የንቅናቄ መድረኩ የተዘጋጀዉ በወርልድ ቭዥን ኢትዮጵያ አሶሳ ቅርንጫፍ የገንዘብ ድጋፍ ሥሆን ከማነቃቂያ መድረክ በኋላ የቀጣይ ጊዜያት ሥራዉን ለመስራት የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት መድረኩ ተጠናቋል ።

በዳንጉር ወረዳ የማንቡክ ጤና ጣቢያ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በተለይ በጤና ጣቢያው በሪፈራል ኦዲት ዙርያ እየተሰሩ ...
27/05/2026

በዳንጉር ወረዳ የማንቡክ ጤና ጣቢያ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በተለይ በጤና ጣቢያው በሪፈራል ኦዲት ዙርያ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ከኢሉ የሴቶችና ህፃናት የተቀናጀ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ድጋፋዊ ጉብኝት አድርገዋል።

ድጋፋዊ ጉብኝቱ በክልሉ ጤና ቢሮ በክሊኒካል ዳይሬክተሬት ስር የሚሰራው የጤና አገልግሎት በጤና ኬላ-ጤና ጣቢያ-ሆስፒታሎች ትስስር በማጠናከር ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ተገልጸዋል።

ከጤና ጣቢያዎችም የተነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ተቀብሎ የሚመለከተው የባለድረሻ አካላት በችግሮች ዙርያ ተነጋግሮ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ እየተሰራ መሆኑን የክልል ጤና ቢሮ የጤና አገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ክብሩ ከበደ በድጋፋዊ ጉብኝት ወቅት ተናግረዋል።

የጤና ተቋት የእርስ በእርስ ትስስርን በማጠናከር በዘርፉ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ለማጠናከር የክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች እያደረጉት ያለው ድጋፋዊ ጉብኝት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

የክልሉ ጤና ቢሮ!

ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሀ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንኳን ለ1...
26/05/2026

ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሀ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሀ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ!! በዓሉ የፈጣሪያችንን መልካም ፈቃድ የምንፈፅምበት፤ ደግነትንና አዛኝነትን በተግባር የምንገልጥበት የበረከት በዓል ይሁንልን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዒድ ሙባረክ!!!

!كل عام وأنتم بخير بمناسبة عيد الأضحى المبارك لعام 1447هـ
نسأل الله أن يكون هذا العيد المبارك مناسبة نحقق فيها إرادة خالقنا الطيبة، ونجسد فيها قيم الخير والرحمة والعطف في واقع حياتنا، وأن يعيده علينا جميعًا
بالبركات والسلام.
عيد مبارك

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር በመተከል ዞን የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ከማሻሻል ባለፈ የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።(ግልገል በለስ:-ግንቦ...
26/05/2026

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር በመተከል ዞን የእናቶች እና ህጻናትን ጤና ከማሻሻል ባለፈ የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።

(ግልገል በለስ:-ግንቦት 18/2018) ማህበሩ በመተከል ዞን በተመረጡ ወረዳዎች የእናቶችና ህጻናት ጤና ከማሻሻል ባለፈ የስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ግንዛቤ በማስፋት ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር በፓዊ ወረዳ ከመንደር 7 ቀበሌ ከተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በእናቶች ስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ማህበሩ በወረዳው የእናቶችና ህጻናትን ጤና ከማሻሻል ባለፈ የቤተሰብ ዕቅድ እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የፓዊ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ቀልቤሳ ተሬሳ፤ በዞኑ አራት ወረዳዎች ማለትም ፓዊ፣ ዳንጉርና ወምበራ ወረዳዎች የተመረጡ ጤና ተቋማት ላይ ለእናቶች ምቹ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል።

ማህበሩ የእናቶችና ህጻናትን ጤና በዘላቂነት ከማሻሻል ባለፈ፣ የቤተሰብ እቅድ እና ጾታን መሰረት አድርገው የሚደርሱ ጥቃቶችን በመከላከል ረገድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አስተባባሪው ይሄን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በመተከል ዞን ጤና መምሪያ የእናቶችና ህጻናት ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብደላ ኢብራሂም፤ መንግስት ጤናው የተጠበቀ ትውልድ ለማፍራት በሚያደረገው ጥረት ውስጥ ማህበሩ እያከናወነ ያለው ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበሩ የጤና ተቋማት በሙሉ አቅም ወደ ስራ እንዲገቡና የተሟላ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስተባባሪው አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር የእናቶችና ህጻናትን ጤና ከማሻሻል ባለፈ በዞኑ በተመረጡ ወረዳዎች ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድን በማቋቋም የህክምና አገልግሎት በመስጠት የሙያ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል ሲል የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ዘገባ ያመላክታል።

በክልሉ የበሽታ ዳሰሳና ቅኝት ለማጠናከር  የሁሉም  ባለድርሻ  አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ  መሆኑን  የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ  ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ። የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ  ክልል ጤና ቢሮ ...
26/05/2026

በክልሉ የበሽታ ዳሰሳና ቅኝት ለማጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ክላስተር አሁናዊ ሁኔታ ላይ መክሯል ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥርና ምላሽ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መብራቱ በጉኖ የተለያዩ ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ በሽታዎች እና በክልሉ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል በክልሉ የበሽታ ዳሰሳና ቅኝት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል ።

ይህን ሥራ ዉጤታማ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አቶ መብራቱ ተናግረዋል።

የዉይይቱ ዓላማ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በግንቦት 09 /2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ (DRC) እና በዩጋንዳ በቡንዲቡግዮ (Bundibugio) በቫይረስ ዝርያ የሚመጣ የኢቦላ ቫይረስ በሽታ መከሰቱን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ መሠረት በክልሉ በሽታውን ለመከላከል እንደሀገር ባሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችና እንደክልል መደረግ በሚገባቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ዙሪያ ለመወያየትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ።

የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ከፍተኛ የስርጭት እና የሞት ምጣኔ ያለው በሽታ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው በንክኪ በቀላሉ, የሚተላለፍ በመሆኑ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ መብራቱ አስረድተዋል ።

ምንም እንኳን በሽታው ከተገኘባቸው አገራት ጋር ቀጥተኛ የድንበር ግንኙነት ባይኖረንም በተለያዩ ምክንያት የህዝብ ለህዝብ እንቅስቃሴ በመኖሩ በክልሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች የየብስ መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች የልየታ እና የቅኝት ስራዎች በማጠናከር፣የጤና ተቋማት ዝግጁ በማድረግ እንዲሁም የላቦራቶሪ አቅምን የማሳደግ እንዲሁም አስፈላጊው የህክምና ግብአት አቅርቦት ላይ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለመስራት የዉይይት መድረኩ መዘጋጀቱን አቶ መብራቱ አክለዉ ገልፀዋል።

ይህንን ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል ደግሞ የሁሉም አካላት ርብርብ አስፈላጊ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንደአለባቸዉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።

በዉይይቱ ላይ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ኢንሰቲትዩት ባለሙያዎች፣የክልል ጤና ቢሮ የሚመለከታቸው ክፍሎችና በክልሉ በጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

Address

Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul Gumuz Health Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Benishangul Gumuz Health Bureau:

Share