13/05/2026
#በ ክቡር ከንቲባ አቶ አብዶ አሊ ድጋፍ በጤና ተቋሙ ተነሳሽነት በ 3 ወር ውስጥ የተመዘገቡ
ተቋሟዊ ስኬቶች*****
1 ፡ የማህበረሰቡን የመድሀኒት አቅርቦቱን ለማሻሻል ከተቋሙ የቦርድ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በHealth care finance የ 600 ሺህ ብር መድሃኒት በመግዛት ተቋሙ ለህብረተሰቡ በቂ አለመሆኑን በመረዳት ከ ኢ /መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር አመታዊ ውል በመጠቀም
በዱቤ (Credited RDF drug) 702,474.34 ብር መድሃኒት በአጠቃላይ በዚህ 3 ወር የ 1,302,474 ብር ( አንድ ሚልዮን ሶስት መቶ ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰባ አራት ብር ) ለህብረተሰቡ አቅርብዋል
2፡ የተገልጋዮቻችንን እንግልት ለመቀነስና ለአላስፈላጊ ወጪ ለማዳን ተቋሙ ከ ኢ/ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በ ብድር መልክ የ 477,635.77 ከ 20 በላይ የምርመራ ውጤት የሚያወጣ የ CBC ማሽን የአመት የራሱ ከሆነ ኬሚካል ጋር አቅርበን ለህብረተሰቡ በቅናሽ ዋጋ አግልግሎት እንዲያገኝ አድርገናል
3፡ በጀትን ጥገኛ ከመሆን ወጥተን ከተማው ውስጥ ያሉትን ባለሀብቶችንና ድርጅቶችን በማስተባበር ለ 12 አመት ምንም አይነት እድሳት ተደርጎለት የማያውቅ ጤና ተቋም በገንዘብ ደረጃ 420000 ሺህ የሚገመት የቀለም እድሳት ፤ የመብራት መስመር ጥገና ፤ እንዲሁም የፈራረሱ ኮርኒሶችን እድሳት እንዲህ ባማረ መልኩ በ 2ወር ጊዜ ገደብ ውስጥ አከናውነናል
4 ፡ እንደ ሀገር የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ተቋሙ እንዲሁ በራሱ ተነሳሽነት በመጀመር ክቡር ከንቲባ አቶ አብዶ አሊ የተቋሙን ተነሳሽነት በማድነቅ በገንዘብ ደረጃ 100ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ተቋሙም ከተማው ላይ ካሉ ባለሀብቶች ጋር በመነጋገር በተጨማሪም ተቋሙ ለጀመረው ስራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ከተቋሙ ሰራተኞች ደሞዝ ላይ በገንዘብ 400 ብር ድጋፍ በማስድረግ በገንዘብ ደረጃ 370000 ብር በማስተባበር የአረንጓዴ አሻራችንን እንዲህ ባማረ መልኩ አሳክተናል
5፡ ተቋሙ አግልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በፍጥነት እልባት ለመስጠት ከዚህ ቀደም ተደርጎ የማይታወቅ ማንኛውም ተገልጋይ እጁ ላይ ባለ ስልክ አስተያየት የሚሰጥብትን ቀላልና ምቹ ድህረገጽ (Software) ፈጥሮ QR ኮዱን ፎቶ ከተቋሙ ግድግዳዎች ላይ ፎቶ በማንሳት አስተያየታቸውን
እየለገሱ ለህብረተሰቡ የተሻለ አግልግሎት በመስጠት
ላይ እንገኛለን****