17/06/2026
አንዲት እናት በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላቸው በርህራሄ የተሞላ ህክምናና እንክብካቤ በመርካታቸው የሆስፒታሉን ባለሙያዎች አመሰገኑ።
************************************
ወ/ሮ ከበቡሽ ካማ ይባላሉ በታቦር ክፍለከተማ የፋራ ቀበሌ ሀላዴ መንደር ነዋሪ ናቸው። አንገታቸው ላይ ከ11 አመታት በላይ የቆየና በየጊዜው እያደገ የመጣው የእንቅርት በሽታ እንቅልፍ ነስቷቸዋል። በዕለታት አንድ ቀን በመኖሪያ አካባቢያቸው ባለውና በየጊዜው ህመም ሲያጋጥማቸው በሚታከሙበት ሆስፒታል ለመታየት ወሰኑ። በወቅቱ ሆስፒታል ሲደርሱ የነበረው በርህራሄ የተሞላ መስተንግዶ አስደሳችና ቤታቸው የሆነ ያህል ይሰማቸው እንደነበር እኚህ እናት ይገልፃሉ። በሆስፒታሉ የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም በሆነው ዶ/ር ይገረም አሰፋ ቀጠሮ ይሰጣቸዋል። ነገር ግን ተጓዳኝ ስር የሰደደ ህመም መኖርና ሎሎች ቀዶ ህክምናውን ከባድ የሚያደርጉ ጉዳዮች በመኖራቸው ህክምናውን ለማድረግ ፍርሀት ያድርባቸዋል።
የቀዶ ህክምናው ቡድን እሳቸውን ለማከም በጊዜው ቢገኝም በተደጋጋሚ በተቀጠሩበት ቀን ሳይገኙ ቀርተዋል። ቡድኑም ሳይሰለች እኚህን እናት በትዕግስት ህክምናውን እንዲያደርጉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ምክር ሰጥቷቸዋል። በመጨረሻም በቡድኑ ምክር በመስማማታቸው ውስብስብ የሆነውን ህክምና በተሳካ ሁኔታ ሊያደርጉ ችለዋል። ከህመማቸው በማገገማቸው ምክኒያት እና ባለሙያዎቹ ባሳዪዋቸው ፍቅርና እንክብካቤ የሲዳማ ብሄር ባህል የሆነውን ሻፌታ ይዘው መጥተው ለባለሙያዎቹ እንዲሁም ለሆስፒታሉ ምስጋና አቅርበዋል።