Haramaya University

Haramaya University Haramaya University is one of the oldest universities in Ethiopia. It is located 5 km from Haramaya, welcome
(1)

08/05/2026
08/05/2026
07/05/2026

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረሪ ክልል ለሚገኘው ጂኒኤላ ጤና ጣቢያ የኮምፒዩተር ድጋፍ አደረገከሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ በቀረበ የድጋፍ ጥያቄ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ጤና ጣቢያው አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማ...
06/05/2026

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረሪ ክልል ለሚገኘው ጂኒኤላ ጤና ጣቢያ የኮምፒዩተር ድጋፍ አደረገ

ከሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ በቀረበ የድጋፍ ጥያቄ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ጤና ጣቢያው አሰራሩን ዲጂታላይዝ በማድረግ የአሰራር ቅልጥፍናን ለማምጣት እንዲያግዘው ሃያ ኮምፒተሮችን ለጤና ጣቢያው ሃላፊ አስረክቧል፡፡

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና ኢንዱስትሪ ትስስር አስተባባሪ አቶ ኢብሳ አሊይ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰቡን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ለጤና ጣቢያው የተደረገው የኮምፒውተሮች ድጋፍ መንግስትም በ2030 ስራዎችን ሙሉለሙሉ ዲጂታላይዝድ ለማድረግ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጤና ጣቢያው የተገልጋዮችን መረጃዎች ዲጂታላዝድ ለማድረግ የጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የጤና ጣቢያው መረጃዎች ዲጂታላይዝድ ከሆኑ በሚፈለጉበት ጊዜ በቀላሉ መገኘት ስለሚችሉ ለጤና ምርምር ስራዎች በመረጃ ማዕከልነት የሚያገለግል መሆኑንና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በስልጠናና በቁሳቁስ ድጋፍ ጤና ጣቢያውን እያገዘ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረሪና በሶማሊ ክልሎችነ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጤና መረጃን የማዘመንና የጤና ተቋማት ዲጂታል ኢትዮጵያን እንዲያሳኩ የመረጃ አያያዛቸውን እንዲያዘምኑ እገዛ እያደረገ መሆኑን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጻህፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር መምህር ጥላሁን ሽፈራው ገልፀዋል፡፡

በሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ የጂኒኤላ ጤና ጣቢያ ሃላፊ አቶ መሃመድ ኢብራሂም ኮምፒውተሮቹን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ጤና ጣቢያው ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተለያዩ ስራዎችን አብሮ እየሰራ መሆኑን አስታውሰው፤ የጤና ጣቢያውን አሰራር ዲጂታላይዝድ አድርጎ ለማዘመንና የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ሃያ ኮምፒውተሮችን በድጋፍ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡ አወቀ አያልነህ
ምስል፡ ቲዎድሮስ ሊሻን
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት
ሚያዚያ 2018 ዓ/ም

   and Knowledge Exchange /2026
06/05/2026


and Knowledge Exchange
/2026

  #ረቡዕ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም  ፡30 ጀምሮ
04/05/2026


#ረቡዕ ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም

፡30 ጀምሮ

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረማያ ሀይቅ ተፋሰስ ጽህፈት ቤት የዓለም የመሬት ቀንን በስልጠና አከበረበየዓመቱ አፕሪል 22 የሚከበረውን የዓለም የመሬት ቀን "ሀይቃችን አይናችን" በሚል መሪ ቃል በ...
03/05/2026

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረማያ ሀይቅ ተፋሰስ ጽህፈት ቤት የዓለም የመሬት ቀንን በስልጠና አከበረ

በየዓመቱ አፕሪል 22 የሚከበረውን የዓለም የመሬት ቀን "ሀይቃችን አይናችን" በሚል መሪ ቃል በሐረማያ ሀይቅ ውሃ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለአካባቢው ማህበረሰብ በመስጠት ቀኑ ተከብሯል።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሀይቅ ተፋሰስ ልማት አስተባባሪ አቶ ዲኔ ረሺድ እንደገለፁት የመሬት ቀንን ምክንያት በማድረግ የተቀናጀ የተረፈ ምርት ምርትና ቁሻሻ አወጋገድ እና የአካባቢ የፅዳት አያያዝን በተመለከተ ለተማሪዎችና ለአካባቢው ነዋሪዎች ስልጠና ሰጥተዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሕብረት አባላት ፣ የማያ ከተማ ወጣቶች ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ በማህበር የተደራጁ ሰዎች ስልጠናውን እንደወሰዱ አቶ ዲኔ ተናግረዋል::

ስልጠናውን የሰጡት መምህር መሀመድ ሙሳ አካባቢን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የተቀናጀ የቁሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓትን መከተል ስለሚየስፈልግ ይህን ለማድረግ ማህበረሰቡን በማሰልጠን ንፁህ አካባቢን እውን ለማድረግ የማህበረሰብ ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና መስጠታቸውን ገልፀዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ስራ ያለ ማህበረሰቡ ተነሳሽነት ዕውን ሊሆን ስለማይችል ሰልጣኞች ያገኙትን ግንዛቤ ለአካባቢው ነዋሪዎች በማዳረስ ከቤት የሚወጡ ቁሻሻዎችን በተቻለ መጠን ጥቅም ላይ መልሰው እንዲውሉ በማድረግ አካባቢያቸውንና ሐረማያ ሀይቅንም የመጠበቅ ስራ እንዲሰሩ ስልጠና መሰጠቱ አቶ መሀመድ አብራርተዋል።

በሀይቁ ተፋሰስ ውስጥ ያለአግባብ የሚጣለው ቁሻሻ በጎርፍ ወደ ሀይቁ ውስጥ የሚገባ በመሆኑ የሀይቁን ብዝሀ ህይወት የሚረብሽና ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ የቁሻሻ አወጋገድ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የገለፁት አሰልጣኙ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን በሀይቁ ላይ ከፍተኛ አደጋ እንደሚደቀን አስረድተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት ወ/ሮ ሀስና አብደላና አቶ አብዲ መሀመድ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ለሌሎች እንደሚያካፍሉ ጠቁመው ዩኒቨርሲቲው ሐረማያ ሀይቅን ለመጠበቅ እያደረገ ያለው ድጋፍ በማገዝ አብረው መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

ዘጋቢ፦ ጃፈር ዩሱፍ
ፎቶግራፈር፦ ፎአድ አህመድ

Address

Haramaya
Bate
138

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haramaya University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Haramaya University:

Share