Fano Fano

Fano Fano Ayenew YouTube እንረዳዳ

24/10/2023

የጎጃም ፋኖ ዕዝ የአቋም መግለጫ !

እኛ በጎጃም እዝ የምንገኝ የአማራ ፋኖዎች የጎጃም ዕዝ ምስረታን ተከትሎ የሚከተሉትን ባለሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ከስምምነት ላይ በመድረስ አጽድቀናል ።

1ኛ ሁሉም በጎጃም ፋኖ ዕዝ የሚመራ ፋኖ የፋኖነትን ስነ ባህሪ የተላበሰ መሆን እንዳለበት ተስማምተናል ።
2ኛ ሁሉም ፋኖ የአማራን ህዝብ የሚያስቀይም እና የሚያስከፋ ተግባር የሚፈጽሙ አካላትን አጥብቀን የምንታገል መሆናችንን ተስማምተናል

3ኛ ሁሉም በዕዙ የሚመራ የፋኖ አባል እና መስራች በዕዙ አዛዦች እየተመራ ተልዕኮውን እና ግዳጁን እንደሚፈጽም ተስማምተናል።
4ኛ. እኛ የዕዙ መስራቾች የትኛውንም ዘር ቋንቋ ሀይማኖት ህዝብ ወይንም ማንነት በጠላትነት ፈርጀን ያልተነሳን መሆኑን በማረጋገጥ ተስማምተናል ።
5ኛ እኛ የእዙ መስራቾች የአባቶቻችንን ጥበብ በመጠቀም የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በመቀልበስ እና የአያቶቻችንን ቤተመንግስት በመረከብ ነጻ የሆነ የህዝብ አስተዳደር ለመመስረት ተስማምተናል ።
6ኛ እኛ የዕዙ መስራቾች ሁሉንም የአማራ ህዝብ በማሳተፍ እና ሁሉን አቀፍ ተጋድሎ በማድረግ ወደፊት የምንገሰግስ መሆኑን ተስማምተናል ።
7ኛ እኛ የዕዙ መስራቾች እና መላው የፋኖ አባል የሰራዊቱን ውስጣዊ አንድነት የሚሸረሽር የገባውን ቃል ኪዳን የሚክድ የሚዘርፍ እና ንጹሀንን የሚያሳድድ ግለሰብም ይሁን ቡድን ፈጽሞ የማንታገስ መሆኑን ተስማምተናል።

ድል ለአማራ ህዝብ !

24/10/2023

Address

123
Dangila
1234

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fano Fano posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Fano Fano:

Shortcuts

Share