Amhara Public Health Institute D/Markos branch

Amhara Public Health Institute D/Markos branch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amhara Public Health Institute D/Markos branch, Medical and health, D/Markos, Debre Mark'os.

17/04/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

17/04/2026
የአብክመ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደማ  ቅርንጫፍ የላቦራቶሪ ጥራት  ማሻሻያ ፕሮግራም ደረጃ በደረጃ ማሻሻያ ፕሮግራም   አፈጻጸሙን በመገምገም የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በደብ...
31/03/2026

የአብክመ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደማ ቅርንጫፍ የላቦራቶሪ ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ደረጃ በደረጃ ማሻሻያ ፕሮግራም አፈጻጸሙን በመገምገም የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በደብረ ማርቆስ ከተማ የምክከር መድረክ አካሄዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የአብክመ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ ድረስ ድልነሣ የላቦራቶሪ አገልግሎት ለህብረተሰብ ጤና አደጋዎች እና ጥራት ላለው የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አስተዋፅኦው የጎላ እንደሆነ ገልፀው ሁሉም በየደረጃው በሃላፊነት መምራት እና ሙያዊ ግዴታውን መወጣት እንዳለበት አመላክተዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪው ክፍል ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ እመቤት ሳህሌ የላቦራቶሪ ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራሞች ለፕሮግራም ብቻ ሳይሆን ለላቦራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እና በየደረጃው ያሉ ሃላፊዎች ግብዓትና የሰው ሀይል በማሟላት ተከታታይ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ተግባራትን በውጤታማነት ለመፈፀም በቁርጠኝነትና በተነሳሽነት መስራት ይገባል ያሉት ዳይሬክተሯ በላቦራቶሪ አገልግሎት ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ሁሉም ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር አቶ ድረስ ድልነሣ አክለውም የሚካሄዱ ስልጠናዊ ግምገማዎችን መሰረት በማድረግ በተቋም ርስ በርስ በመማማር እና ራስን በማብቃት በተመደብንበት ሙያ ብቁ አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ጥራት ያለው የላቦራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ግብዓት ለማሟላት ጥረት በማድረግ ለስራው ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሩ ጤና ተቋማት በክፍሉ በቂ ባለሙያ በመመደብ፣ ሃብት በማፈላለግ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በላቦራቶሪው መሻሻል እንዲሳተፍ የምክክር መድረክ በማዘጋጀት በቅንጅት በመስራት እንዲሁም አመራሮች ድጋፍና ክትትል በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ የሆስፒታል ስራ አስኪያጅ፣ የላቦራቶሪ ሃላፊና የጥራት ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች : የላቦራቶሪ አስተባባሪዎች ና የላቦራቶሪ የጥራት ቁጥጥር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

24/01/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ 04

24/01/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ 06

የአማራ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት- ደብረ ማርቆስ  ቅርንጫፍ የላቦራቶሪ የውጭ ጥራት ቁጥጥር ስራን ለማሻሻል  የምክክር መድረክ አካሄደ በጤና ተቋማት የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ስታንዳርድን መ...
14/12/2025

የአማራ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት- ደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ የላቦራቶሪ የውጭ ጥራት ቁጥጥር ስራን ለማሻሻል የምክክር መድረክ አካሄደ

በጤና ተቋማት የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ስታንዳርድን መሰረት አድርገው እንዲተገበሩ ለማድረግ የላቦራቶሪ የውጭ ጥራት ቁጥጥር አስፈላጊ በመሆኑ የምስራቅ ጎጃም ዞንና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊዎች: የቲቢ:የወባ እና የፈውስ ህክምና ኦፊሰሮች :የሆስፒታል ስራ አስኪያጅ:የላቦራቶሪ አስተባባሪና የላቦራቶሪ የጥራት ቁጥጥር እንዲሁም ፖስታ ቤት በተገኙበት የጋራ ምክክር ተካሄዷል ።

የላቦራቶሪ የውጭ ጥራት ቁጥጥር ስራ ቀደም ብሎ ሲተገበር የቆዬ በላቦራቶሪ አገልግሎቶች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳጊ የሆነ ለውጥ ያመጣ ተግባር ቢሆንም ለውጡ ከስታንዳርድ አኳያ በሚፈለገው ልክ ስላልሆነ ይህን ችግር ለመፍታት የላቦራቶሪ ስታንዳርዱን መሰረት አድርጎ በወቅቱ በየደረጃው በኃላፊነት ተወስዶ መሰራት እንዳለበት አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

አጠቃላይ የህክምና ላብራቶሪ አገልግሎቱን ለማሻሻል በላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር : በውጭ ጥራት ቁጥጥር የስላይድ አሰባሰብ እና አጓጓዝን በተመለከተ የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ገለጻና ውይይት ተካሂዷል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ምላሽና የማጠቃለይ ሀሳብ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።

https://www.who.int/emergencies/disease-outbreak-news/item/2025-DON585
22/11/2025

https://www.who.int/emergencies/disease-outbreak-news/item/2025-DON585

On 12 November 2025, WHO noted a press release from the Ethiopian Ministry of Health (MoH), and the Ethiopian Public Health Institute (EPHI), announcing suspected viral hemorrhagic viral fever (VHF) in Jinka town, South Ethiopia Regional State, Ethiopia. On 14 November 2025, the Ministry of Health o...

08/11/2025

Address

D/Markos
Debre Mark'os

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Public Health Institute D/Markos branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share