Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital

Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital Hiwot Fana Comprehensive University Hospital (HFCSUH) is a central teaching and referral hospital under Haramaya University.

It serves an estimated 20-30 million population in Eastern Ethiopia.

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የ COMS-A አባል በመሆን የምስክር ወረቀት አገኘ።"የአፍሪካን የጤና ግብረ ኃይል ላልተረጋገጠ መጻኢ ጊዜ ማዘጋጀት፡ አጋርነትን፣ ቴክኖሎጂን...
11/07/2026

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የ COMS-A አባል በመሆን የምስክር ወረቀት አገኘ።

"የአፍሪካን የጤና ግብረ ኃይል ላልተረጋገጠ መጻኢ ጊዜ ማዘጋጀት፡ አጋርነትን፣ ቴክኖሎጂን፣ ፈጠራን እና አመራርን በመጠቀም" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሲካሔድ በቆየው የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ( ) ላይ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የ COMS-A አባል በመሆን የአባልነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱን በይፋ ተቀብሏል።

COMS-A በአህጉራችን የዲጂታል ፈጠራን በማስፋፋት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን (AI) በመጠቀም፣ ግብዓቶችን በጋራ በመካፈል እና የትምህርት ሥርዓቶችን ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ የጤና ትምህርትን ለመለወጥ የተቋቋመ ስትራቴጂካዊ ጥምረት ነው።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ ኢትዮጵያ በሕክምና ትምህርት ውስጥ የዲጂታልና የ AI ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ይህ ጉባኤ የአፍሪካን የጤና ሙያ ትምህርት ለማጠናከር፣ በሀገራት መካከል ያለውን የእውቀትና የልምድ ልውውጥ ለማሳደግ፣በትምህርት፣ በምርምር እና በፈጠራ ዙሪያ ዘላቂ አህጉራዊ ትብብርን ለማጠናከር ጠቃሚ እድል የሚፈጥር ነው።

በዚህ አህጉር አቀፍ ጉባኤ ላይ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅን በመወከል የህክምና ትምህርት ቤት ኃላፊ፣ መምህራን ፣ ተመራማሪዎች እና የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት የተገኙ ሲሆን ጉባኤውም ከሰኔ 29/2018 ጀምሮ ለ ሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ በትናንትናው እለት ሐምሌ1,2018 በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ
ሐምሌ 2/2018

10/07/2026
Stakeholders Emphasize the Need for Institutional Coordination to Ensure Food Safety in Ethiopia; PIONEER Project Set fo...
09/07/2026

Stakeholders Emphasize the Need for Institutional Coordination to Ensure Food Safety in Ethiopia; PIONEER Project Set for Multi-Institutional Implementation

Various institutions working in food-related sectors in Ethiopia must coordinate their efforts to prevent and address the health, social, and economic challenges arising from poor food safety.

This message was emphasized during a consultative workshop held in Addis Ababa by Haramaya University’s Foodborne Disease Surveillance and Survey (PIONEER) project, in collaboration with government agencies and partner organizations focused on food safety.

Dr. Desalegn Admasu, the Principal Investigator of the PIONEER project, stated that the initiative aims to establish a surveillance system to monitor and control foodborne diseases across the country. Led by Haramaya University, the project collaborates with Arba Minch University, Debre Berhan University, and St. Paul's Hospital Millennium Medical College. It will utilize the Health and Demographic Surveillance System (HDSS) sites managed by these higher education institutions.

Dr. Desalegn explained that foundational preparatory activities conducted over the past few months included training data collectors, engaging with community representatives, establishing technical advisory groups at the HDSS sites, and forming a national steering committee led by the Ministry of Health.

Despite the presence of multiple government institutions focused on food safety in Ethiopia, the lack of a unified platform has previously hindered collaborative data synthesis and exchange. The PIONEER project aims to address this gap by bringing stakeholders together to ensure that data on food safety and foodborne diseases are effectively integrated for the benefit of the nation.

Dr. Desalegn further elaborated that instead of allowing research findings to go unused, the project will provide actionable data and policy inputs capable of influencing national policy directions. Over the next four years, the project will work toward establishing a shared understanding of how Ethiopia's foodborne disease surveillance system should operate, facilitating information exchange to prevent and reduce foodborne illnesses.

Dr. Masresha Tessema, Director for Nutrition, Environmental Health, and Non-Communicable Diseases Research Directorate at the Ethiopian Public Health Institute (EPHI), noted that foodborne health risks are increasing both globally and nationally, making institutional coordination essential. He emphasized that the PIONEER project strengthens the surveillance and response system by linking research institutions with national bodies.

Dr. Masresha highlighted that the data generated by the project will serve as a crucial input for EPHI's national surveillance operations. He added that subsequent efforts will focus on utilizing these baselines to establish legal and regulatory frameworks for implementation at both federal and regional levels.

Sector experts participating in the workshop underscored that political leadership and commitment from policymakers are critical for transforming research findings into practical applications that benefit the public and the nation. Participants pledged their support for transitioning the PIONEER project from its preparatory phase to full implementation.

The workshop also featured researchers from George Washington University (USA), one of the project's supporting institutions, who shared international experiences regarding disease surveillance and response systems.

Photograher: Behailu Girma
Haramaya University Public and International Relations

በኢትዮጵያ የምግብ ደህንነትን ለማስጠበቅ የተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀበኢትዮጵያ በምግብ ዙሪያ የሚሰሩ በርካታ ተቋማት በተናጠል የሚያከናውኑትን ስራ በማቀናጀት በምግብ ደህንነ...
09/07/2026

በኢትዮጵያ የምግብ ደህንነትን ለማስጠበቅ የተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

በኢትዮጵያ በምግብ ዙሪያ የሚሰሩ በርካታ ተቋማት በተናጠል የሚያከናውኑትን ስራ በማቀናጀት በምግብ ደህንነት መጓደል ምክንያት የሚከሰቱ የጤና ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመከላከልና ለማቃለል በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ወለድ በሽታዎች ክትትልና ቅኝት (ፓዮኒር/PIONEER) ፕሮጀክት በምግብ ደህንነት ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊና አጋር ተቋማት ጋር በአዲስ አበባ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የፕሮጀክቱ ዋና ተጠሪ ዶክተር ደሳለኝ አድማሱ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በሀገሪቱ የምግብ ወለድ በሽታዎችን ለመቆጣጠርና ለመከታተል የሚያስችል የቅኝት (Surveillance) ስራን የሚያከናውንና በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መሪነት ከአርባ ምንጭ እና ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ጋር በመሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ስር ባሉ የጤናና ስነ-ህዝብ ዳሰሳ (HDSS) ጣቢያዎች በመጠቀም የሚተገበር ነው።

ፕሮጀክቱ ባለፉት ወራቶች የመረጃ ሰብሳቢዎችን ማሰልጠን ፣ በማህበረሰብ ደረጃ ካሉ ተወካዮች ጋር መተዋወቅ፣ በጣቢያዎቹ ላይ የቴክኒክ አማካሪ ቡድኖችን መመስረት እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር የሚመራ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የማደራጀት መሰረታዊ ስራዎች በዝግጅት ወቅት መከናወናቸውን ዶክተር ደሳለኝ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ በምግብ ደህንነት ዙሪያ የሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ቢኖሩም መረጃዎችን በጋራ የሚያቀናጁበትና የሚለዋወጡበት ወጥ የሆነ መድረክ ስላልነበረ የፓዮኒር ፕሮጀክት እነዚህን ባለድርሻ አካላት በአንድ መድረክ ላይ በማገናኘት በምግብ ደህንነትና በምግብ ወለድ በሽታዎች ዙሪያ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ተቀናጅተው ለሀገር ጥቅም እንዲውሉ ያደርጋል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ የምርምር ውጤቶችን ብቻ ይዞ ከመቀመጥ ባለፈ የሀገሪቱን የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፉና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ መረጃዎችንና የፖሊሲ ግብዓቶችን እንደሚያቀርብ ዶክተር ደሳለኝ አብራርተዋል።

በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ በምግብ ምክንያት የሚከሰቱ ህመሞችና የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችሉ መረጃዎች የሚለዋወጡበትንና የኢትዮጵያ የምግብ ወለድ በሽታዎች ቅኝት እንዴት መስራት እንዳለበት የጋራ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚያከናውኑ የፕሮጀክቱ ተጠሪ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስርዓተ ምግብና የአካባቢ ጤና እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ማስረሻ ተሠማ በበኩላቸው በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብ ምክንያት የሚመጡ የጤና አደጋዎች እየጨመሩ በመሆናቸው ተቀናጅቶ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የፓዮኒር ፕሮጀክት የምርምር ተቋማትን ከሀገር አቀፍ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር የቅኝትና ምላሽ ስርዓቱን የሚያግዝ መሆኑን ዶክተር ማስረሻ ጠቁመው በፕሮጀክቱ የሚወጡት መረጃዎች የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሚያከናውነው ሀገር አቀፍ የቅኝት ስራ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆኑና በቀጣይም ይህንን መነሻ በማድረግ ሀገሪቱና ክልሎች የሚተገብሩት ህግ እንዲሆን እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደጠቆሙት የምርምር ተቋማት የሚያወጧቸው የጥናት ውጤቶች ወደ ተግባር ተለውጠው ህዝብና ሀገርን እንዲጠቅሙ ለማድረግ የፖለቲካ አመራሮችና የፖሊሲ አውጭዎች ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ተሳታፊዎቹ አያይዘውም የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ያስጀመረው የፓዮኒር ፕሮጀክት ከዝግጅት ምዕራፍ አልፎ ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲሸጋገር በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በመድረኩ ላይ ፕሮጀክቱን ድጋፍ ከሚያደርጉ ተቋማት መካከል የአሜሪካው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችም ተገኝተው በበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ልምድ አካፍለዋል።

ፎቶግራፈር፦ በሀይሉ ግርማ
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 91.5

05/07/2026
በሐረር ከተማ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ማገገሚያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል የስምምነት ውል ተፈረመ።​የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል...
04/07/2026

በሐረር ከተማ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ማገገሚያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል የስምምነት ውል ተፈረመ።

​የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ከኤስ ኦ ኤስ (SOS) የህፃናት መንደር ሐረር ፕሮግራም እና ከሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የሶስትዮሽ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ በሆስፒታሉ ውስጥ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው የሴቶች እና ህፃናት እንክብካቤ፣ ህክምና እና ማገገሚያ ማዕከል ግንባታን ለማከናወን ያለመ ነው።

​የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕይወት ፋና ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቪ ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ መሀመድ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ ቀደም ሲል በሆስፒታሉ ደረጃ ሲሰጥ የነበረውን የጥቃት ሰለባዎች የመደገፍ አገልግሎት ይበልጥ በሰፊው ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል።

ዶክተር አህመድ አክለውም፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው የቴክኖሎጂ ጫና በተለይም ከዲጂታል ስልኮች አጠቃቀም ጋር ተያይዞ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ የጥቃት አይነቶችና መጠኖች እየሰፉ በመምጣታቸው፣ ችግሩን ለመከላከል ከአጋር አካላት ጋር በጋራ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

​የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብዲ አሚን በበኩላቸው፣ የዚህ ደህንነቱ የተጠበቀ ማገገሚያ ማዕከል ግንባታ ሐረርን ከፆታዊ ጥቃት የፀዳች የማድረግ ራዕይን ለማሳካት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ተጎጂዎች አስፈላጊውን ህክምና፣ እንክብካቤ እና ፍትህ የሚያገኙበት አሰራር እንደሚዘረጋ የጠቀሱት ዶክተር አብዲ፤ የክልሉ ጤና ቢሮ ማዕከሉ ተገንብቶ አገልግሎት እንዲጀምር ሀብት በማፈላለግ፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት እና የክትትልና ቁጥጥር የአመራርነት ሚናውን እንደሚወጣ አስታውቀዋል። ይህ ተግባር የሰብአዊነት ስራ በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

​በ SOS ህፃናት መንደር ኢትዮጵያ የሐረር ፕሮግራም ሎኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አስፋው በበኩላቸው፣ ተቋማቸው በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸው፤ ከሆስፒታሉ በተረከቧቸው 10 ክፍሎች ላይ ምቹና ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል ለመገንባት 16,500 ዩሮ በጀት መመደቡን ይፋ አድርገዋል።

​ማዕከሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃና ተጎጂዎች የተቀናጀ ድጋፍ የሚያገኙበት እድል እንዲፈጠር ተቋማቸው በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አቶ ሙሉቀን አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ ታደለ ጥላሁን
ፎቶ ግራፈር፦ በሐይሉ ግርማ
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን

Dhaabbata Gargaarsa Daa'immanii (SOS children's Villages) Biiroo fayyaa Naannoo Hararii fi Yuunivarsiitii Haramaayaa Hos...
03/07/2026

Dhaabbata Gargaarsa Daa'immanii (SOS children's Villages) Biiroo fayyaa Naannoo Hararii fi Yuunivarsiitii Haramaayaa Hospitaala Hunda galeessa Addaa Hiwoot Faanaa waliin hojjechuuf sanada waliigaltee waliin mallattessan.

Waliigaltichii mirga daa'immanii fi dubartoota akkasumas miidhaa koorniyaa bu'uureeffate ittisuuf gargaarsa seeraa,wal'aansa,dinagdee fi xiinsammuu saaxilamtootaaf kennuf Hospitaala Hiwoot Faanaatti giddu gala ijaarudhaan hojiitti galchuf waliigaltee mallattaa'e ta'u isaa ibsamera.

Daayreektara Dhaabbata Gargaarsa Daa'immanii (SOS children's Villages) damee Harar obbo Muluqan Asfaaw yaada kennanin miidhaa daa'immanii fi dubartoota irraa gahuu ittisun nageenya isaani mirkaneessuf dhaabbatichi pirojekti gara garaa naannoo Harariitti hojjechaa akka jiru ibsun kaayyoon waliigaltee kanaas dhaabbatichi miidhaa koorniyaa bu'uureeffate hambisuuf qooda fudhattoota waliin qindoominaan waliin hojjechuf waliigaltee taasifame ta'u himaniru.

Daayreektara olaanaa Yuunivarsiitii Haramaayaa kolleejjii saayinsii fayyaa fi wal'aansa fi Hospitaala Hiwoot faanaa Dr.Ahmad Mahammad waliigaltee mallattaa'e ilaalchisun yaada kennanin Hospitaala Hiwoot Faanaa saaxilamtoota miidhaa koorniyaa bu'uureeffatef deeggarsa wal'aansa fi seeraa kenna akka ture eerun,waliigaltichii tajaajila kana karaa fooyya'insa qabun fi qindoominaan kennuuf kan dandeesisu ta'u himaniru.

Hogganaan Biiroo fayyaa Naannoo Hararii Dr.Abdi Amin gamasaanitin dubartootaa fi daa'imman saala isaaniin walqabatee miidhaa qaamaa fi xiinsammuuf saaxilaman kunuunsaa wal'aansa fi eegumsa seeraa argatani akka dandamatan kan dandeessisu dhaabbata gargaarsa daa'immanii SOS children village waliin ta'un Hospitaala Hiwoot Faanaatti giddu gala ijaaruf sanada waliigalte mallattaa'e ta'u dubbataniru.

Gabaasa: Bahaayiluu Mokonin
Suuraa: Bahaayiluu Girmaa
Waxabajjii 26/10/2018
kutaa sab-qunnamti Yuunivarsiitii Haramaayaa koollejjii saayinsii fayyaa fi wal'aansa

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚተገበረው "የPIONEER ፕሮጀክት" ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምግብ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር...
03/07/2026

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚተገበረው "የPIONEER ፕሮጀክት" ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምግብ ወለድ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለተጀመረው አገር አቀፍ የቅኝት (PIONEER) ፕሮጀክት ስኬት ሲባል፣ በመስክ ላይ ለሚሰማሩ የጤና ባለሙያዎችና መረጃ ሰብሳቢዎች የሶስት ቀናት ተግባራዊ ስልጠና በሐረር ከተማ ተሰጥቷል።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር ፣ ተመራማሪ እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ደሳለኝ አድማሱ እንደገለጹት፤ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መሪነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአራት ሳይቶች (ቡታጅራ ፣ ደብረብርሀን ፣ አርባምንጭ እና ሐረርጌ) የሚተገበረው ይህ ታላቅ ፕሮጀክት፣ ለቀጣይ የፖሊሲ ውሳኔዎች ትልቅ አገራዊ ግብዓት የሚሆን ነው።

ጥናቱ መደበኛ ምርመራ ሳይሆን እጅግ የላቀ የዘረመል (genetic) ጥናት በመጠቀም የበሽታውን ምንጭ በግልጽ ለመለየት ያስችላል። በሆድ ህመም የተጠቁ ሰዎችን፣ በገበያ የሚሸጡ ጥሬ ምግቦችን (ሰላጣ፣ ጎመን ወዘተ)፣ የስጋ፣ የወተትና የእንቁላል ምርቶችን እንዲሁም የቤት ለቤት ናሙናዎችን መሰብሰብን ያጠቃልላል ብለዋል ።

በሐረርጌ ከቀረሳ ሳይቶች የተወጣጡት ሰልጣኝ የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው፤ ስልጠናው ከምግብ ዝግጅትና ከእንስሳት ተረፈ-ምርቶች ጋር ተያይዘው በሚመጡ የበሽታ ምንጮች ላይ አዲስ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልጸው፣ ናሙናዎችን በጥራት ለመሰብሰብ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ይህ አገር አቀፍ ጥናት በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በዶክተር ደረጄ ዱጉማ በሚመራ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የቅርብ ክትትል የሚደረግበት ሲሆን፤ በቀጣይ መንግስት የታለሙ የመከላከያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ትልቅ የፖሊሲ ግብዓት እንደሚሆን ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ ታደለ ጥላሁን
ፎቶ ግራፈር፦ በሐይሉ ግርማ
ሰኔ 25/2018 ዓ.ም
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን

Pirojektin Hordoffii Dhibee nyaatarra Maddu Itoophiyaa "PIONEER" Leenjii Dandeetti Raawwachistummaa cimsu Sassaabdota Ra...
02/07/2026

Pirojektin Hordoffii Dhibee nyaatarra Maddu Itoophiyaa "PIONEER" Leenjii Dandeetti Raawwachistummaa cimsu Sassaabdota Ragaa Pirojektichaaf kenne.

Dhibee gara garaa fi summii nyaataan dhufuu qorachuun tarsimoo mootummaa Itoophiyaa baase ( National food safety master plan) akka milkaa'uuf ragaa qulqullina qabu qabatamaa dhiheessun kan hojjetu fi Yuunivarsiitii Haramaayaan kan hogganamu Pirojektin Hordoffii Dhibee nyaatarra Maddu Itoophiyaa( Ethiopia Foodborne Disease Surveillance Project) Sassaabdota Ragaa buufataalee sirna hordoffii Dimoograafii fayyaa Harargee (Harerge HDSS site), hawaasa fi buufata fayyaa keessa ogeessota ragaa sassaabanif leenjii hubannoo cimsu guyyota sadif kenne jira.

Pirojektichi qulqullina nyaataa fi ittisa irratti xiyyeeffachun dhibeewwan nyaatarra maddan kannen akka garaa kaasaa,haqqee,dhukkubbi garaa akkasumas keemikaaloota fi baakteeriyaa miidhaa geessisuu karaa saayinsawaa ta'en qorachun sadarkaa biyyaatti galtee tarsimoo dhibee nyaatarra maddan to'achuuf oolu qorannoodhaan hojjechaa akka jiru fi
kaayyoon leenjii kanas sassaabdota ragaa kaayyoo fi ragaa hojii pirojektichaaf barbaachisu sirritti hubatani ragaa qulqulluu akka sassaaban dandeettii raawwachistummaa isaani cimsuf leenjii qophaa'e akka ta'e Yuunivarsiitii Haramaayaa kolleejjii saayinsii fayyaa fi wal'aansatti barsiisaa fi qorataa akkasumas qindeessaa Pirojektichaa kan ta'an Dr.Dasaalany Admaasu (Associate Proffesor) ibsaniru.

Ogeessonni leenjii kanara hirmatan tokko tokko yaada kennanin leenjiin kennamee irraa toftaalee sassaabbi ragaa dhibee nyaatarra maddu ilaalchisee beekumsaa fi barumsa guddaa kan argatan tahuu ibsun bu'aawwan ragaa qorannoo pirojektichaaf barbaachisuu karaa sirrii fi qulqullina qabun sassaabuf caalmaatti kan isaan jajjabeessu ta'uu dubbataniru.

Gabaasa: Bahaayiluu Mokonin
Suuraa: Bahaayiluu Girmaa
Waxabajjii 24/10/2018
kutaa sab-qunnamti Yuunivarsiitii Haramaayaa koollejjii saayinsii fayyaa fi wal'aansa

Address

Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share