AWI ZONE Health Department

AWI ZONE Health Department ጤና ለሁሉም፣ሁሉም ለጤና!!!

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር  ጤና መምሪያ በጤና ተቋማት የሚካሄደውን የአትክልትና ፍራፍሬ የተከላ መርሐግብር ሰኔ 30/2015 ዓ/ም አስጀመረ ። የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አየለ አልማው በባንጃ...
07/07/2023

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ በጤና ተቋማት የሚካሄደውን የአትክልትና ፍራፍሬ የተከላ መርሐግብር ሰኔ 30/2015 ዓ/ም አስጀመረ ። የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አየለ አልማው በባንጃ ወረዳ በዲንካራ ጤና ጣቢያ በመገኘት የተከላ መርሐ ግብሩን አስጀምረዋል ። በመርሐ ግብሩ የጤና መምሪያ ባለሙያዎች፣ የባንጃ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ተገኝተው ተከላ አካሂደዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ተከላውን ያስጀመሩት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ አልማው እንደገለፁት የአገሪቱ የጤና ፓሊሲ መከላከልን መሠረት ያደረገ በመሆኑ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት ለህሙማን ምቹ ፣ ሳቢና የተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በብሄረሰብ አስተዳደሩ በሚገኙ አጠቃላይ የጤና ተቋማት ላይ አረንጓዴ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ለማካሄድ ታቅዶ በባንጃ ወረዳ በዲንካራ ጤና ጣቢያ ማስጀመራቸዉን ተናግረዋል ።
በጤና ተቋማት የሚተከሉ ችግኞች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን አትክልትና ፍራፍሬ በመትከል እና አረንጓዴ አካባቢን ለመፍጠር መሆኑን የገለፁት መምሪያ ኃላፊው በዛሬው እለት የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በሌሎች 48 ጤና ጣቢየዎችም እንዲካሄድ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ የጤና ጣቢያው ማህበረሰብ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርግ በማሳሰብ የዕለቱን መርሐግብር ተጠናቋል።
FOR A BETTER TOMORROW,PLANT MORE TREES TODAY!!!
ጤና መምሪያ (የህዝብ ግንኙነት ክፍል)
ሰኔ 30/2015 ዓ.ም

የአዊ ብሔረሰብ  አስተዳደር ጤና መምሪያ የ4ኛ ዙር የCOVID_19 ክትባት እና የHPV ክትባት  አድቮኬሲ አካሔደ ፡፡የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ የማህፀን በር ካንሰር እና 4ኛ ...
02/05/2023

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ የ4ኛ ዙር የCOVID_19 ክትባት እና የHPV ክትባት አድቮኬሲ አካሔደ ፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ የማህፀን በር ካንሰር እና 4ኛ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ለመስጠት የምክክር መድረክ በ19/8/2015 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ አካሄደ። እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ልጃገረዶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት እና ከ18ዓመት በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ-19 ክትባት እንደሚሰጥ የአዊ ብሄረሰብ ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡
እድሜያቸው አስራ አራት ለሆኑ ልጃገረዶች ከሚያዚያ 24 -27 የማህፀን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት በየትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ሲሆን በተጠቀሰው የእድሜ ክልል ውስጥ ሁነው ትምህርት ላይ የማይገኙ ዜጎች ካሉም በየአቅራቢያቸው ካሉት ትምህርት ቤቶች በመሄድ ክትባቱን መውሰድ እንዳለባቸውም አሳስቧል፡፡
በውይይት መድረኩ እንደተገለጸው የማህፀን ጫፍ ካንሰር በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ መሆኑን የተብራራ ሲሆን ከካንሰር በሽታወች ሴቶችን በመግደል ሁለተኛ ደረጃን የያዘ በመሆኑና አስከፊ መሆኑን በመጥቀስ በሽታውን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄው ክትባት በመሆኑ ልጃገረዶች የመጣላቸውን እድል እንዲጠቀሙ ሁሉም በየደረጃው መረባረብ እንዳለበት ጥሪ ተላልፏል፡፡
በተያያዘም ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 03 የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ እና በገዳይነቱ የታወቀውን የኮሮና ወረርሽኝ በሽታን ለመከላከል ዋና መፍትሔ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ በመሆኑም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች 4ኛ ዙር የኮቪድ 19 የመከላከያ ክትባት ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 3/2015 ዓ/ም እንደሚሰጥ ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በምክክር መድረኩ የብሄረሰብ አስተዳደር ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪዎች ፣የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ከንቲባዎች ፣ለሀይማኖት አባቶች፣የጤና መምሪያና የወረዳ የጤና ጽ/ቤት የሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

የዊ ብ/አስ ዞን ጤና መምሪያ
ሚያዚያ 23/2015 ዓ.ም

የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ የአብከመ ጤና ቢሮ ለወለቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን በተለያዩ ሙያዎች ለመቅጠር በዞን ጤና መምሪያችን ምዝገባ ይካሄዳል፡ ፡ ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ቢሮ ቁጥር 9...
20/04/2023

የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ
የአብከመ ጤና ቢሮ ለወለቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ዞን በተለያዩ ሙያዎች ለመቅጠር በዞን ጤና መምሪያችን ምዝገባ ይካሄዳል፡ ፡ ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ቢሮ ቁጥር 9 እንድትመዘገቡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡ ፡

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ የ7ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ፣ የሃይጅን ሳኒቴሽን እና የአይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ችግር ላለባቸዉ ህክምና በሚል ሲ...
12/04/2023

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ የ7ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ፣ የሃይጅን ሳኒቴሽን እና የአይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ችግር ላለባቸዉ ህክምና በሚል ሲካሄድ የነበረዉ የንቅናቄ መድረክ ተጠናቀቀ።
በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምርያ አዘጋጅነት በግምጃ ቤት ከተማ ከመጋቢት 16-17/2015 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረዉ የንቅናቄ መድረክ የስራ ስምሪትና የቀጣይ አቅጣጫወችን በመስጠት ተጠናቋል።
በመድረኩ የብሔረሰቡ ዋና አስተደዳሪ ፣ ዋና አፈ-ጉባኤ፣ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ፣የሚመለከታቸው መምሪያ ኃላፊዎች፣ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የጤና ጣቢያ ዳይሬክተሮች ፣ የወሳኝ ኩነት የቡድን መሪዎች ፣ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያዎች ፣የሀይጅንና ሳኒቴሽን ኦፊሰሮች ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የሆስፒታል ሥራስኪየጆች፣ የጤና መምሪያ ባለሙያዎች፣ በጤናው ሴክተር የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት በአጠቃላይ 313 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ታድመዋል ።
የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ አልማው የግምገማና የንቅናቄ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት የመክፈቻ ንግግር በብሔረሰብ አስተዳደር ባለፉት 7ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መሻሻል የታየባቸው ፕሮግራሞች ማለትም የሕፃናት ክትባት ፣ የእናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትልና በሰለጠነ ባለሙያ ወሊድ ፣ በሥርዐተ ምግብ የቫይታሚንና ዲዋርሚንግ ፣ በኤች. አይ. ቪ ምርመራና የህክምና ትስስር ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈፃፀሞች መሻሻል የታየባቸው መሆኑን ጠቅሰው በክፍተት በወሊድ ምክንያት የእቶች ሞት ማጋጠሙ፣የሕፃናት ህክምና አገልግሎት አለመሻሻል ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የዘላቂነት ችግር፣ የሀይጅንና ሳኒቴሽን ጽዱ ከተማ መፍጠር አለመቻል፣ ትራንስፎርም ያደረጉ ወረዳዎች ውስን መሆን፣የቁጥጥር ሥራዎች የትኩረት ማነስ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የግባት አቅርቦት ችግር በጉድለት የታዩና ቀጣይ መሻሻል እንዳለባቸው አብራርተዋል። ሌላው የሴክተሩ ዋና ተግዳሮት የሆነው የበጀት እጥረትና በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት የግንባታ መቋረጥ /መጓተት መሆኑን አስገንዝበዋል። ሃላፊው አያይዘውም አመራሩ እና የጤና ሞያተኛዉ ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ፣ የሃይጅን ሳኒቴሽን እና የአይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ችግር ላለባቸዉ ህክምና በቀሪ ወራት በንቅናቄ የሚሰሩ መሆናቸውን ለተሳታፊዎች አስረድተዋል።
መድረኩ ሁለተኛ ቀን ቀጥሎ የዋለ ሲሆን የብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ፣ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ እና በመምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ አልማው ውይይቱን መርተዋል ።
በውይይቱ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አለማየሁ ገበየሁ እንደገለፁት ለአገልግሎት አሰጣጥ ትኩረት ተሰጦ እንዲሰጥ እና የሃይጅንናሳኒቴሽን ስራዉ ሳይሳካ ወደ ኋዋላ እንዳይመለስ አመራሩ በጥብቅ ክትትል መሥራት እንዳለበትና የጤናው ሴክተርም ከመምሪያ እስከ ልማት ቡድን ያለውን አመራርና ባለሙያ በማነቃነቅ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኜ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ወረዳዎችን በማመስገን በቀጣይ ቀሪ ወራት በአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዬች ውይይት ከዞን እስከ ቀበሌ እንዲካሄድ ፣ የመድኃኒት አቅርቦ እጥረት እንዲሻሻል፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ወደ ተግባር እንዲገባ፣ የሃይጅን ሳኒቴሽን እና የአይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ችግር ላለባቸዉ ቀዶ ህክምና በንቅናቄ እንዲሰራ የሥራ መመሪያ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል።
ቀለሙ ደሴ (የጤና መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ተጠሪ)
መጋቢት 2015 ዓ.ም
ግምጃ ቤት

11/04/2023

Good communication is an important part of all relationships and is an essential part of any healthy partnership!!!
Wel-come to this public health relation page of ZHD

Address

ZHD
Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AWI ZONE Health Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share