Seid Hussen Drug Store

Seid Hussen Drug Store ጥራት ደህኝነታቸው የተጠበቁ የህክምና መድኃኒቶች ኮስሞቲክ?

20/03/2026
16/02/2026

የፋርማሲስቱ የፍቅር ደብዳቤ

[ Dispensary ቆሜ antibiotic ልትገዢ ለመጣሽው ልጅ....]

ዛሬ interpret የማደርግልሽ special prescription ምን ያህል እንደ narcotic እና psychotropic drugs ወድጄሽ addicted እንደሆንኩብሽ ለመግለጽም ጭምር ነው።

የኔ diazepam አንቺን ሳላስብ እንቅልፍ አልወስድክ አለኝ!! በእርግጥ tolerance እንደፈጠርሽብኝ ልንገርሽ አስብና አንደበቴ ይተሳሰራል ወይስ ketamine ልወጋና ልቀባጥርልሽ?? ደግሞ ከርቀት ሳይሽ በውበትሽ ተገርሜ atropine እንደተወጋ pt ዓይኔን የማፈጠው ነገርስ። ግን ምን ያደርጋል ከኩራትሽ የተነሳ የማሳልፈው nightmare የተሞላበት ሕይወት Efavirenz ነሽ እንዴ ብዬ እንድጠራጠር አድርጎኛል።

ፍቅርሽን በdonation ካልሰጠሽኝ በስተቀር እንደ ድህነቴ በprocurement purchase ላደርግሽ አልችልም። ደግሞ አንቺ ላይ invest ያደረኩትን reimburse የሚያደርገኝ ያለ እንዳይመስልሽ። አንቺ የኔ Brand ምን አለበት በኔ አቅም Afford ብትደረጊ አንቺ? ለእኔ እንደ promethazine 1st line እና potent እንደሆንሽ ነበር የማስበው፤ አንቺ ግን Antidote እንደሌለው Barbiturate toxicity ሆነሻል!!

ቢሆንም እንደ Digoxin ጠባብ therapeutic index የለኝም፤ በሰፊው Pencillin ልቤ እጠብቅሻለሁ ግን የማልደብቅሽ ነገር ቢኖር አንቺን በቀን QID ማሰቡ ታክቶኛል። endpoint እንደ ሌለው reaction እስከ መቼ Titrate ልታደርጊኝ አስበሻል?? የ Tubocurarine structure ማንበብ እራሱ እንዳንቺ አልታከተኝም።

ልቤን በኩራትሽ mortal and pestle sizun reduce፤ በንቀትሽ base እና በግልምጫሽ spatula levigate አድርገሽ ointment ካደረግሽኝ ሰነባብተሻል።

ከLeujocum aestivum የተገኘውን Galanthamine ካልወሰድኩ ስለምረሳ ይህንንም ፅፌልሻለሁ። Minimal Change disease(MCD) steroid sensitive እንደሆነ እኔም ላንቺ sensitive ሆኛለሁ ግን ከpoor prgnosis ጋር!!

ቆይ አንቺ ማነሽ?? ሰውስ 'እንደ Erythromycin መራራ ናት ትቅርብክ!' ለምን አለኝ?? ለምንድነውስ BBB Cross እያደረግሽ CNS Disturbance የምታመጭብኝ??

ወይ ደግሞ ልብሽን ስጭኝና Macerate አድርጌው ፍቅርን Extract ላድርግ.. ካንቺ ጋር ሆኜ የምኖረው QALY በእርግጥም አንቺ ከሌለሽበት ሕይወት ይሻላል።

አስቢበት እኔ Chiral ስለሆንኩ dosage form ቀይሬ ሌሎች ጋር መሄድ አያቅተኝም። አዎ አስቢበት እንደ TDF+3TC+ EFV ዕድሜ ልኬን ላስብሽ አልፈልግም። እኔ በcGMP ስለምመራ Flexible እሆንልሻለሁ።

አታስቢ ፍቅርሽን ከinfusion ወደ bolus ብትቀይሪው Red man syndrome አይፈጠርብኝም። የፍቅርሽ Bioavailabilty 100% እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ ልነግርሽ እወዳለሁ። ስለዚህ የኔ ፍቅር Updated, Recent and Reliable የሆነ Goal of Therapyሽን ንገሪኝና Treatment approach ወስኜ ላንቺ ያለኝን Pharmaceutical care ላሳይሽ።

ያንቺው አፍቃሪ: ከፋርማሲ

15/02/2026
ስጋን በጋዜጣ ጠቅልሎ መሸጥ ለጤና ያለው ጉዳት ‼ ጋዜጣ ለንባብ እንጂ ምግብን ለመጠቅለል ተብሎ ስላልተመረተ፣ ከስጋ ጋር በቀጥታ ሲገናኝ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳቶች ያስከትላል፦📌1. የኬሚ...
11/02/2026

ስጋን በጋዜጣ ጠቅልሎ መሸጥ ለጤና ያለው ጉዳት ‼

ጋዜጣ ለንባብ እንጂ ምግብን ለመጠቅለል ተብሎ ስላልተመረተ፣ ከስጋ ጋር በቀጥታ ሲገናኝ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳቶች ያስከትላል፦

📌1. የኬሚካል መርዛማነት (Chemical Toxicity)

በጋዜጣ ህትመት ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቀለሞች (Inks) እንደ ሊድ (Lead) እና ካድሚየም (Cadmium) ያሉ ከባድ ብረቶችን ይይዛሉ። ስጋው እርጥበት ስላለው እነዚህ ኬሚካሎች በቀላሉ ከወረቀቱ ተላቀው ወደ ስጋው ይገባሉ። እነዚህ ንጥረ ነገሮች በሰውነት ውስጥ ከተከማቹ ለካንሰር፣ ለኩላሊት እና ለጉበት በሽታ የመጋለጥ እድልን ይጨምራሉ።

📌2. የማይክሮብ ብክለት (Microbial Contamination)

ጋዜጣ ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ እጃችን ላይ እስኪደርስ ድረስ በብዙ እጆችና ባልተጠበቁ ቦታዎች ያልፋል። በዚህ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባክቴሪያዎችን፣ ቫይረሶችን እና አቧራዎችን ይሸከማል። ስጋው በእነዚህ ጀርሞች ከተበከለ ለተቅማጥ፣ ለታይፎይድ እና ለሌሎች የምግብ ወለድ በሽታዎች ይዳርጋል።

📌3. የምግብ ጥራትና ጣዕም መለወጥ

የጋዜጣው ቀለምና ኬሚካል ወደ ስጋው ስለሚገባ የስጋውን ተፈጥሯዊ ጣዕም፣ ሽታና ቀለም ይለውጠዋል። ይህ ደግሞ የምግቡን ጥራት ዝቅ ያደርገዋል።

📌 ለፌስታል አማራጭ ምን መጠቀም ይቻላል?

የፌስታል እገዳ አካባቢን ለመጠበቅ የታለመ ቢሆንም፣ ስጋን በጤናማ መንገድ ለመያዝ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይሻላል፦

* የምግብ መጠቅለያ ወረቀቶች (Parchment/Wax Paper): ለምግብነት ተብለው የተመረቱና ምንም ዓይነት ቀለም የሌላቸው ወረቀቶች።
* የአሉሚኒየም ፎይል (Aluminum Foil): ስጋው ሳይበከል እንዲቆይ ይረዳል።
* የፕላስቲክ ዕቃዎች (Food-grade Containers): በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ የቤት ውስጥ መያዣዎችን ይዞ በመሄድ ስጋን መግዛት።
* ንጹህ ጨርቅ: በደንብ የታጠበና የደረቀ ንጹህ ጨርቅ ለጊዜያዊ መሸፈኛነት ሊያገለግል ይችላል።

📌 ማሳሰቢያ: "ጋዜጣው ይታጠባል" ወይም "ስጋው ሲበስል ኬሚካሉ ይጠፋል" የሚሉ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ። ኬሚካሎቹ ወደ ስጋው ውስጠኛ ክፍል ስለሚገቡ በሙቀት በቀላሉ አይጠፉም።
መረጀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ነው።

ይህ እንደ መድሀኒት የሚዋጠው ክኒን ካሜራ ነው። 24 ስዓት አንጀት ውስጥ ቆይታ አድርጎ መረጃ ከሰጠ በኋላ በዛው ይወጣል።ሳይንቲስቶች አሁን ይህን የሚዋጥ ክኒን በመጠቀም የምግብ መፈጨት ችግ...
17/01/2026

ይህ እንደ መድሀኒት የሚዋጠው ክኒን ካሜራ ነው። 24 ስዓት አንጀት ውስጥ ቆይታ አድርጎ መረጃ ከሰጠ በኋላ በዛው ይወጣል።

ሳይንቲስቶች አሁን ይህን የሚዋጥ ክኒን በመጠቀም የምግብ መፈጨት ችግሮችን መመርመር ይችላሉ። ያልታወቀ የደም ማነስ ወይም የተጠረጠሩ የውስጥ ደም መፍሰስ ላለባቸው ታካሚዎች፣ የካፕሱል ኢንዶስኮፒ - ብዙውን ጊዜ "የክኒን ካሜራ" ተብሎ የሚጠራው - ዶክተሮች መደበኛ ሂደቶች በቀላሉ ሊደርሱባቸው የማይችሉትን የምግብ መፈጨት ትራክት ክፍሎችን እንዲመረምሩ ያስችላቸዋል።

ሂደቱ በትንሽ ካሜራ እና ብርሃን የተገጠመለት የቫይታሚን መጠን ያለው ካፕሱል መዋጥን ያካትታል። በተፈጥሮው በምግብ መፍጫ ሥርዓት ውስጥ ስለሚንቀሳቀስ፣ በሰከንድ እስከ ስድስት ፍሬሞች ድረስ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምስሎች ይይዛል፣ ይህም የትንሹ አንጀትን ዝርዝር፣ 360 ዲግሪ እይታ ይሰጣል - ወደ 20 ጫማ የሚጠጋ ርዝመት።

ሂደቱ ማደንዘዣ የማያስፈልገው ስለሆነ፣ ታካሚዎች ወዲያውኑ መደበኛ እንቅስቃሴዎችን መቀጠል ይችላሉ። ካፕሱሉ ባዮፕሲ መውሰድ ባይችልም፣ ምስሎቹ ዶክተሮች እንደ ክሮንስ በሽታ ወይም ትንሽ የአንጀት ዕጢዎች ያሉ ችግሮችን በትክክል እንዲያገኙ ይረዷቸዋል። ካፕሱሉ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል ሲሆን በተለምዶ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተፈጥሮ ከሰውነት ይወጣል።

Address

Kelela

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Seid Hussen Drug Store posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Seid Hussen Drug Store:

Shortcuts

Share