Kamba Town Administration Health Office

Kamba Town Administration Health Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kamba Town Administration Health Office, Alternative & holistic health service, kamba, Kemba.

‎   _ዘመቻ_ለጤና_ባለሙያዎች_ለጤና ኤክስቴንሽን_ባለሙያዎች_እና_ለባለድርሻ_አካላት_ስልጠና_መሰጠት_ተጀመረ።‎‎መስከረም 9/2018 ዓ.ም(ካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጥ/ጽ/ቤት)።‎ ‎በዕለቱ ...
19/09/2025

‎ _ዘመቻ_ለጤና_ባለሙያዎች_ለጤና ኤክስቴንሽን_ባለሙያዎች_እና_ለባለድርሻ_አካላት_ስልጠና_መሰጠት_ተጀመረ።

‎መስከረም 9/2018 ዓ.ም(ካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጥ/ጽ/ቤት)።

‎በዕለቱ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የካምባ ከተማ አስ/ር መንግሥት ዋና ተጠሪ ፣የካምባ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር ፣ የካምባ ዙሪያ ወረዳ መንግሥት ዋና ተጠሪ እና የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፍ ጨምሮ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርጓቸዋል።

‎በንግግራቸው የትራኮማ በሽታ የሚያስከትለው የዓይነ ስውርነት ችግር ምን ያህል አስከፊ እንደሆነ በመረዳት የመድሐኒት ዕደላ ዘመቻው ከወትሮው በተለየ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ ሊተግበር እንደሚገባ ጥቅሰው ለመድሃኒት ዕደላ ዘመቻ ተግባራዊነት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎በንግግሩ የካምባ ከተማ አስ/ር መንግሥት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ ይስሀቅ ዮሐንስ ባስተላለፉት መልዕክት
‎ ዘመቻው በጥራትና በፍጥነት በታቀደው ልክ እንዲጠናቀቅ ሰልጣኞች ከሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡እንዲሁም መመሪያ መልዕክት እና ለሎችን በጤና መስክ የነበሩ ጉዳዮችን አስምሮ አንስቷል።

‎ቀጥሎ የካምባ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ አዴ አለሙ የትራኮማ በሽታ መከላከያ መድሃኒት እደላው ቤት ለቤት በመጎብኘት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው በዘመቻው በሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ እና ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ገልጿል፡፡ አስተዳዳሪ አያይዞም ትራኮማ የዕይታ መቀነስ እና ዓይነስውርነትን የሚያስከትል በሽታ ነው ተብሏል።

‎በመቀጠል የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፍ አቶ ኢዮብ ደርቤ ባስተላለፉት መልዕክት (የማህበረሰብ ዐቀፍ መድኃኒት ዕደላ ዘመቻ) zithiromax መድሃኒት የዓይን ማዝ ብቻ ሳይሆን ለሎች በርካታ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያ ዓይነቶችን የማከም አቅም ያለ መድሀኒት ነው ብሏል። አያይዘውም ዘመቻው ለተከታታይ 11 ቀን የሚቆይ ስሆን ድርጅቱም ኦርቢስ እንተርናሽናል በ3 ፕሮግራሞች ዙሪያ የሚሰራ ስሆን እነርሱም :-(1) ገጠርን ያማከለ አጠቃላይ የአይን ጤና ክብካቤ።(2) በመከላከልና በማከም ላይ ያቶኮረ የአይን ጤና አገልግሎት አቅም ማጎልበት የአይን ጤና ጥናትና ግንዛቤ ማስጨበጫ።(3) እንዲሁም የአይን ማዝ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ስሆን የድርጅቱ ማጠንጠኛ የትራኮማን ማጥፋት ወይም ኮምፕርሄንስቭ(comprehensive) አገልግሎት መስጠት ነው ብሏል።

‎ኃላፍው አያይዘውም ትራኮማ (የዓይን ማዝ) በባክቴሪያ አማካይነት የሚመጣ ተላላፊ የሆነ ዓይነስውርነትን የሚያስከትል የዓይን ሕመም ስሆን የበሽታው አምጪ ተህዋስያን ቺላሚዲያ የትራኮማቲስ (chlamydia Trachomatis) እየተባለ የሚጠራ ባክቴሪያ ነው ብሏል።

‎ይህ በእንዲህ እንዳለ MDA(mass drug administration) ማህበረሰብ አቀፍ የትራኮማ መድሃኒት ስርጭቱ አሰፈላጊ ስለሆነ ዕድሜያቸው ከ1-9 ዓመት በሆኑ ህፃናት እና የአፍለኛ ወጣቶች ላይ ትራኮማ ስርጭት ከ5% በታች መቀነስ እና ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ የአይን ቆቦ ሽፋሽፍት ወደ ውሰጥ መቀልበስ ስርጭትን 0.2% በታች ማድረስ።

‎ድርጅቱ በዋናነት የሚሰራው የአይነ ስውርነት ለማጥፋት ስሆን የአለም ጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ መሠረት በአለም ላይ ወደ 2.2 ቢሊዮን የእይታ መቀነስ ችግር ያለባቸው ሰዎች አሉ ከእነዚህ ውሰጥ ከ 1 ቢሊዮን የሚሆኑት ህክምና የሚሹ ናቸው።
‎ #39 ሚሊዮን አይነስውር ሰዎች ይኖራሉ ከእነዚህም ውስጥ 1.4 ሚሊዮን ሕፃናት ናቸው።
‎ #በየአመቱ 1-2 ሚሊዮን የሚሆን እየጨመረ ይገኛል።
‎ #28 ሚሊዮን ሰዎች የሚሆኑት መከላከል ወይንም ማከም በምንችላቸው ምክንያቶች በተከሰቱ ዓይነስውርነት የተጠቁ ናቸው።


‎ስለዚህም በሁሉም ማህበረሰብ ክፍል ከህፃን እስከ አዋቂ ድረስ በሁሉም ቀበሌያት ላይ በከተማም ሆነ በዙሪያ መድኃኒቱን እንድትወስዱ የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት መልዕክቱን ያስተላላፋል።

‎ በጤና ባለሙያ የሚሰጠውን መድኃኒት መውሰድ :- እናደርግ ፣ አይነስውርነትን በጋራ እንከላከል።

‎ምንጭ (የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ሚዲያ )

 ።‎‎ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም(ካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ቤት)‎‎የምሰጠውን ስልጠና አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ላይ የካምባ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር   እና የካምባ ከተማ አስተዳደር መ...
04/09/2025



‎ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም(ካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ቤት)

‎የምሰጠውን ስልጠና አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ላይ የካምባ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር እና የካምባ ከተማ አስተዳደር መንግሥት ተጠሪ ።

‎በቅድሚያ የስልጠናውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካምባ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ቤት ኃላፍ አቶ መሐንዲሱ ቦይና አድርጓል።

‎በመቀጠል ካምባ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር የተከበሩ አቶ አዴ አለሙ በንግግራቸው ጤናማ ማህበረሰብ በመፈጠር የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ይቻላል ብሏል። በመቀጠል የግል፣የአከባቢ፣የመኖሪያ ቤት እና የመጸዳጃ ቤት ንጽሕና በመጠበቅ እንዲሁም አጠቃቀም እና አያያዝን በማዘመን በንጽሕና ጉድለት የሚከሰተው በሽታን መከላከልና መቆጣጠር በቀላሉ እንችላለን በማለት መድረኩን በይፋ አብስሯል።

‎ትኩረት የሚሹ ሃሩራማ በሽታዎች አንዱ ትራኮማ ይባላል ትራኮማ ክላሚዲያ ትራኮማተስ በሚባል በዓይን በማይታይ ጥቃቅን በሽታ አምጭ ተዋህስያን አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን ይህ በሽታ በአብዛኛው የውሃ እጥረት እና የንጽህና ጉድለት ባለባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ይገኛል።

‎ለአብነት ትራኮማ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች:-
‎ህጻናትተና ሴቶች ለትራኮማ ያላቸው ታጋላጭነት ከፍ ያለ ነው።
‎የትራኮማ ምልክቶች፡- ትራኮማ በአብዛኛው ሁለቱንም የዓይን ቆብ የሚያጠቃ ሲሆን፣ በብዛት ግን ምልክቶቹ የሚጠነክሩት በላይኛው የዓይን ቆብ ላይ ነው፡፡

‎ምልክቶች፦
‎ዓይንና የዓይን ቆቦችን የማሳከክ እና የማቃጠል ስሜት
‎ከዐይን እና ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ
‎የዓይን ቆብ ማበጥ
‎ብርሃን መፍራት
‎የዓይን ህመም እይታ ብዥታ

‎የአዐይን ቆብ ወደ ውስጥ መታጠፍ (የህመሙ ደረጃ ከፍ ሲል ጠባሳ እንዲፈጠር፣ እይታ እንዲቀንስ ብሎም ዓይነ-ስውርነት እንዲከሰት ያደርጋል።

‎ ለሎችን ጨምሮ በማጥፋት ዙሪያ ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል።

‎ምንጭ:-የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ሚዲያ ።


 ።‎‎በጋሞ ዞን ካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጥ/ጽ/ቤት የካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጣቢያ መጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው መድኃኒት አወጋገድ ሥነሥርዓት ተካሄደ።‎‎ነሐሴ 23/2017ዓ.ም(ካምባ ከተማ ...
29/08/2025



‎በጋሞ ዞን ካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጥ/ጽ/ቤት የካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጣቢያ መጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው መድኃኒት አወጋገድ ሥነሥርዓት ተካሄደ።

‎ነሐሴ 23/2017ዓ.ም(ካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት።

‎ግዜው ረጅም ግዜ የቆየው መጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን የመድሀኒት አወጋገድ ኮሚቴው በሙላት በመቅረብ ቃል ጉባኤ በመፈራረም የጤና ጽ/ቤት እና የጤና ጣቢያ ግዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን በዛሬው ዕለት በአዋጁ መሠረት የአወጋገድ ሥነሥርዓቱ ተካሂዷል።

‎በቦታው የካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጥ/ጽ/ቤት የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ቁጥጥር ባለሥልጣን ሥራ ሂደት ዳይሬክቶረት ኮሚቴውን በሙላት በመሰብሰብ በአዋጅ መሠረት የአወጋገድ ሥነሥርዓቱን አስፈጽመዋል።

‎በመቀጠል የካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጣቢያ ኃላፍ እንዳሉት መጠቀሚያ ግዜ ያለፈባቸው መድሃኒቶችን የሙያው ባለቤቶች ማለቴ ፋርማሲ ባለሙያዎች በትክክል በመመዝገብ በመለየት በአዋጁ መሠረት ከዚህ በኃላ መፈጸሚ እንዳለበት እና መድኃኒቱ ከአከባቢ አየር ብክለት አኳያ ከሚቃጠል ይልቅ ብቀበር ይመረጣል ብሏል።

‎ምንጭ :- ካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ሚዲያ።

 ፣ሰላምን መደገፍ ነው!ልማትን መደገፍ ነው!ህብረብሔራዊነትን መደገፍ ነው!ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ተምሳሌት!
26/08/2025



ሰላምን መደገፍ ነው!

ልማትን መደገፍ ነው!

ህብረብሔራዊነትን መደገፍ ነው!

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ተምሳሌት!

አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ  ህክምና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛልአርባምንጭ፦ ነሀሴ  20 /2017 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን) Cure ,Blindnes...
26/08/2025

አርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት በመሰጠት ላይ ይገኛል

አርባምንጭ፦ ነሀሴ 20 /2017 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)

Cure ,Blindness project የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህሙማን ነፃ የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል

ህክምናው በተጀመረ በሁለት ቀናት ውስጥ ከ300 በላይ ህሙማን ሙሉ በሙሉ እይታቸው መመለሱ ተመላክቷል።

የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በተለያዩ ጊዜያት በሆስፒታሉ ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው በዚህኛው ዙር ለተከታታይ አምስት ቀናት በ"Cure Blindness Project " አማካኝነት ከ800 አስከ 1000 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ህክምናው እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ዶ/ር አምባቸው አክለውም ህክምናው በተጀመረ በሁለት ቀናት ብቻ ከ300 በላይ ህሙማን ሙሉ በሙሉ እይታቸው መመለሱን ገልፀዋል።

ህክምናውን ለመውሰድ የመጡ ግለሰቦች የአይን ህክምናቸውን ከማድረጋቸው በፊት ተያያዠነት ያለባቸው በሽታዎች በዘመናዊ መመርመሪያ መሳርያዎች በመታገዝ ምርመራና ህክምናም በሆስፒታሉ እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

የህክምናው አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በ"Cure Blindness Project " የሚሸፈን መሆኑንና ከህክምናው በኃላም ለ1 ወር ያህል በያሉበት ድጋፋዊ ክትትል እንደሚደረግ ዶ/ር አምባቸው ገልፀዋል።

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የአይን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ማስረሻ መንግስቱ በበኩላቸው ህክምናው ለሚቀጥሉት 3 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል መሆኑን በመጠቆም ከሌሎች አጎራባች አከባቢዎች በልየታው የተካተቱ በወቅቱ በመገኘት የህክምና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

አያይዘውም ማንኛውም እድሜው ከ40 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ ግለሰብ በሙሉ በየአመቱ የአይን ምርመራ በማድረግ የአይኑን ደህንነት መጠበቅ እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በስፍራው የአይን ህክምናውን ለማግኘት ከጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የመጡት ወ/ሮ ተጴ ተሰማ ለ11 አመታት ሁለቱም አይናቸው በመጋረዱ ሙሉ ለሙሉ ማየት ተስኗቸው ከቤት መውጣት ሳይችሉ መቆየታቸውን በመግለፅ በተደረገላቸው ህክምና እይታቸው በመመለሱ በመደሰት ህክምናውን የሰጡ አካላትን አመስግነዋል።
ዘገባው :-Gamo zone government communication affairs department.

‎ ።‎‎ነሐሴ 19/2017 ዓ/ም(ካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት)‎‎በጋሞ ዞን ካምባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ተግባር  አካል የሆነው የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድ...
25/08/2025

‎ ።

‎ነሐሴ 19/2017 ዓ/ም(ካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት)

‎በጋሞ ዞን ካምባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ተግባር አካል የሆነው የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ በሁሉም ቀበሌ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል።

‎እንደ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ቀበሌ እድሜያቸው 30_49 የሆኑ እናቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ምርመራ፣ልየታና የግንዛቤ ትምህርት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

‎እስካሁን እድሜያቸው 30_49 እድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 105 እናቶች የግንዛቤ ትምህርት ያገኙ ስሆኑ ከነዚህ 43 እናቶች ምርመራውን የተደረጉ ስሆኑ ከተደረጉት 1 እናት ማህፀን ጫፍ ካንሰር positive ሆና የተገነች ስሆን ተገቢ ህክምና ተደርጓላታል።

‎ይህም በእንዲህ እንዳለ ማህፀን ጫፍ ካንሰር አደገኛ ገዳይ ካንሰር ስሆን ያለ ምልክት 15-20 ዓመት መቆየት የሚችል አደገኛ በሽታ ነው። ስለዚህ እድሜያቸው 30-49 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሁሉም እናቶች ወደ ካምባ ከተማ አስ/ር ጤና ጣቢያና ካምባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመሄድ ነፃ ምርመራና ህክምና እንድታገኙ የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ያሳውቃል።

‎ #ካንሰርን በጋራ እንከላከል።
‎ #በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ።
‎ምንጭ:-የካምባ ከተማ አስተዳደር ጤና ጥ/ጽ/ቤት ሚዲያ ።

21/08/2025
በወረዳችን መስከረም 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀን ስካሄድ የነበረው  የትራኮማ በሽታ መከላከያ የመድሃኒት እደላ ዘመቻ አፈጻጸም ማጠቃለያ ተገመገመ።ካምባ ዙሪያ መስከረም 25/2...
05/10/2024

በወረዳችን መስከረም 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀን ስካሄድ የነበረው የትራኮማ በሽታ መከላከያ የመድሃኒት እደላ ዘመቻ አፈጻጸም ማጠቃለያ ተገመገመ።
ካምባ ዙሪያ መስከረም 25/2017 ዓ.ም (ካምባ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት)።

በወረዳዎች እየተካሄደ ባለው የትራኮማ በሽታ መከላከያ የመድሃኒት እደላ በሰባት ቀናት ውስጥ ከ 146 ሺህ በላይ ለሚሆን የማህበረሰብ ክፍል የመድሃኒት እደላ ተደረሽ መደረጉ ታወቀ፡፡

በዘመቻው ሰባት ቀናት ውስጥ በዚትሮምክስ ክኒን 111 ሺህ 204 ሰዎች፣ በዚትሮማክስ ሽሮፕ 32 ሺህ 405 እንዲሆም በቴትራሳይክሊን የአይን ቅባት 3 ሺህ 105 ሰዎች በአጠቃላይ ለ 146 ሺህ 714 ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የመድሃኒት እደላው ተደራሽ መደረጉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል ከዘመቻው ጋር በማቀናጀት ሊሰሩ የሚገባቸው የአይን ቆብ ሽፋሽፍት መታጠፍ (TT Case Screening) 11 ሰዎች እና የቲቢ በሽታ ልየታ በተመለከተ 17 ተጠርጣሪዎች የዘመቻ አካል ሆኖ መገኘቱ በጠንካራ ተገምግመዋል።

በዘመቻው ያጋጠመው ተግዳሮቶች በኮማንድ ፖስቱ በጥልቀት ተገምግሞ ለቀጣይ አቅጣጫ ጭምር ተቀምጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ ይህንን ዕድል ለማህበረሰባችን ጤና ስባል ያመቻቸው orbis international Ethiopia ሰናይ ድርጅት እና የተፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ለማህበረሰባችን ያደረሱ ባለሙያዎችን ጽ/ቤቱ በህዝባችን ስም አመስግነዋል።

በመጨረሻም የዘመቻው ሪፖርት በዚህ ወር መስከረም ወራዊ ሪፖርት በ DHIS 2 በየጤና ኬላው ተጠቃሎ መግባቱን የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮች ክትትል ያደርጉ ዘንድ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል፡፡

ምንጭ :- (ካምባ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት)።

Address

Kamba
Kemba

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kamba Town Administration Health Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share