ረድኤት መድኃኒት መደብር-ኮንሶ/Rediet Drug Store-Konso

  • Home
  • Ethiopia
  • Konso
  • ረድኤት መድኃኒት መደብር-ኮንሶ/Rediet Drug Store-Konso

ረድኤት መድኃኒት መደብር-ኮንሶ/Rediet Drug Store-Konso Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ረድኤት መድኃኒት መደብር-ኮንሶ/Rediet Drug Store-Konso, Medical and health, KONSO, Konso.

ጥርሳችን ውበታችን ነው ጤንነቱን እንጠብቅ፡፡
19/07/2022

ጥርሳችን ውበታችን ነው ጤንነቱን እንጠብቅ፡፡

10/07/2022

ታይፈስ ምንድን ነው?
****************

ታይፈስ ሪኬቲሺያ በሚባል የባክቴሪያ ዝርያ የሚከሰት ሲሆን በቁንጫ፣ ቅማልና መዥገር በመሳሰሉት ተባዮች በምንነከስበት ጊዜ በበሽታው እንያዛለን።

እነዚህ ተባዮች በሚነክሱን ጊዜ የሪኬቲሺያ ባክቴሪያን በነከሱን ቦታ ላይ ይተውታል ከዚያም የነከሱንን ቦታ በምናክበት ጊዜ ቆዳችን ለባክቴሪያዎቹ ክፍት ስለሚሆን ባክቴሪያው በቀዳዳዎቹ በመግባት የደም ዝውውርን ይቀላቀላል፡፡ በደማችንም ውስጥ የማደግና የመራባት ሂደቶቹን ያደርጋል፡፡

የተላያዩ የተባይ አይነቶች ለተለያዩ የታይፈስ በሽታዎች በማጋለጥ የተለያዩ የሪኬቲሺያ ባክቴሪያ ይይዛሉ።

የታይፈስ በሽታ ምልክቶች እንዳለብን የባክቴሪያ ዝርያ ይለያያል፡፡ በአብዛኞቹ በሽተኞች ላይ የሚታዩት ምልክቶች ለአብዛኛው የታይፈስ ዝርያ ዓይነቶች ተመሳሳይ ናቸው።

የዚህ በሽታ ህክምና የሚያተኩረው ኢንፌክሽኑን ለማቆም ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶች መጠቀም ላይ ነው። ያልታከምነው የታይፈስ በሽታ ገዳይ ነው።

በሽታው እንዳይከሰት መከላከል ከህክምናው የበለጠ በጣም ቀላል ነው ስለዚህ መከላከያው አሳተላላፊ የሆኑ ተባዮችን በተለያዩ መንገዶች ማስወገድ ነው።

☑️ የታይፈስ በሽታ መነሻ ምክንያቶች

ታይፈስ እንደ ጉንፋንና ፍሉ በሽታዎች ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም። ተባዮች ለነሱ የሚስማማቸውን የታይፈስ ዝርያ መርጠው በመያዝ ወደ ሰዎች ያስተላልፋሉ።

☑️ የታይፈስ በሽታ ዝርያ ዓይነቶች

1️⃣ ወረርሽኝ ታይፈስ:- መነሻው ሪኬቲሺያ ፕሮዎዛኪ ሲሆን የልብስ ቅማሎች ወደ ሰው ያስተላልፉታል።
2️⃣ ሙሪን ታይፈስ:- መነሻው ሪኬቲሺያ ታይፊ ሲሆን አይጥና የውሻ ቁንጫ ወደ ሰው ያስተላልፉታል።
3️⃣ ስክረብ ታይፈስ:- መነሻው ኦሬንሺያ ቱስቱስጋሙሽ ሲሆን ቅማል ወደ ሰው ያስተላልፉታል።

በባክቴሪያው የተያዙ ተባዮች በሚነክሱን ጊዜ ባክቴሪያውን ወደ እኛ ይሰጡናል ወይም ይጭኑብናል ከዚያም የተነከስነውን ቦታ በምናክበት ጊዜ ባክቴሪያው ወደ ደም ዝውውራችን ውስጥ እንዲገባ እናደርገዋለን ማለት ነው።

☑️ የታይፈስ በሽታ ምልክቶች

የታይፈስ በሽታ ምልክቶች እንዳለብን የታይፈስ ዝርያ ይለያያሉ። የጋራ የሆኑት የታይፈስ በሽታ ምልክቶች እነዚህ ናቸው:-

💎 የራስ ምታት
💎 ከፍተኛ ትኩሳት
💎 የብርድ/ቅዝቃዜ ስሜት
💎 ሽፍታ ናቸው።

አንዳንዴ በወረርሽኝ ጊዜ የሚከሰት የታይፈስ በሽታ የመፍዘዝ ወይም መደንዘዝ ዓይነት ምልክቶች ይታዩበታል።

☑️ የታይፈስ በሽታ ህክምና

ታይፈስ ይኖርብኛል ብለው ይገምታሉ? ሀኪምዎ ሲጠይቅዎ የሚታዩብዎትን ምልክቶችን፣ በቅርቡ ጉዞ ያደረጉ ከሆነ፣ በተባዮች የተነከሱ ከሆነ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ ለሀኪምዎ ይንገሩት:-

🍀ሰዎች በጣም ተጠጋግተው የሚኖሩበት አካባቢ የሚኖሩ ከሆነ
🍀በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ የታይፈስ ወረርሽኝ ካለ
🍀ጉዞ ያደረጉ ከሆነ።

የታይፈስ በሽታ ህክምናን አስቸጋሪ የሚያደርገው ምልክቶቹ ከሌሎች በሽታዎች ማለትም ከደንጉ፣ ወባ እና ብሩሴላ በሽታዎች ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ነው።

የተለያዩ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ይህን በሽታ ለመለየት ይሰራሉ እነሱም:- የደም ምርመራ፣ ኢሚውኖፍሎረሰንስ ቴስት እና ዌስተርን ብሎት ናቸው።

☑️ የታይፈስ በሽታ መድሃኒቶች

ብዙ ጊዜ ታይፈስን ለማከም የምንጠቀምባቸው ፀረ-ባክቴሪያ መድሃኒቶች ሲሆኑ ከነዚህም መካከል:-

🦋 ዶክሲሳይክሊን (Doxycycline)
🦋 ክሎራምፌኒኮል (Chloramphenicol)
🦋 ሲፕሮፍሎክሳሲሊን (Ciprofloxaciline) ናቸው።

☑️ ታይፈስን የመከላከያ መንገዶች
➡️ የግል ንጽህና
➡️ አይጦችን ከአከባቢ ማጥፋት(አይጦች የተለያዩ ተባዮችን ስለሚይዙ)
➡️ ለበሽታው ልንጋለጥ የምንችልበትን አከባቢ መራቅ፡፡
➡️ ዶክሲሳይክሊን እንደ ቅድመ መከላከያ መውሰድ(በሽታው በብዛት በተንሰራፋባቸው አከባቢዎች ለዘመቻ ስንሄድ)

ምንጭ;- ኢትዮ-ጤና

መልካም ዜና ለኮንሶ ማህበረሰብና አከባቢው በሙሉ*****************************************ለማህበረሰባችን የተሻለ የጤና አገልግሎት አማራጭ ለማቅረብ ተዘጋጅተን በኮንሶ ...
03/07/2022

መልካም ዜና ለኮንሶ ማህበረሰብና አከባቢው በሙሉ
*****************************************
ለማህበረሰባችን የተሻለ የጤና አገልግሎት አማራጭ ለማቅረብ ተዘጋጅተን በኮንሶ ካራት ከተማ "የኛ መካከለኛ ክሊኒክ" ከዩኔስኮ አደባባይ ዝቅ ብሎ በቀድሞ የዘውዲቱ ሆቴል ግቢ እንዲሁም "የኛ መድኃኒት መደብር" ከጆሲ ዲጂታል ስቱዲዮ ጎን ከፍተን እንቅስቃሴ ጀምረናል፡፡ ስለሆነም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ከላይ በጠቀስኳቸው ተቋማት በመቅረብ በጤናው ዘርፍ በቂ ልምድ ባላቸው የጤና ባለሙያዎች ትህትናን በተላበሰ መንገድ የተሟላ የጤና አገልገሎት ማገኘት ይችላሉ፡፡

21/05/2022

በቅርብ ቀን ለማህበረሰባችን የተሻለ የህክምና አማራጭ ከጥሩ መስተንግዶ ጋር ይዘን እንቀርባለን፡፡

Address

KONSO
Konso

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ረድኤት መድኃኒት መደብር-ኮንሶ/Rediet Drug Store-Konso posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ረድኤት መድኃኒት መደብር-ኮንሶ/Rediet Drug Store-Konso:

Shortcuts

Share