30/04/2024
(_ወጌሻ_) 😳
ወጌሻ የአጥንት ስብራት እና የመገጣጠሚያ ውልቃት ዘመናዊው የአጥንት ጥገና ሕክምና ባልተጀመረበት ዘመን በልምድ ብቻ እና በጥናት ባልተረጋገጠ ባህላው እውቀቶች ለብዙ ዘመናት ሲሰጥ የነበረ ሕክምና ነው::
በአሁኑ ጊዜ ይህ ሕክምና በሰለጠኑ ሃገራት የቀረ ቢሆንም በሃገራቺንና በአብዛኛው የ አፍሪካ ሃገራት በብዛት አየተዘወተረ ይገኛል ::
የወጌሻ ሕክምና ሊቀር ያልቻለባቸው ምክንያቶች
1, easy accessibility (በቀላሉ በየመንደሩ የሚገኝ መሆኑ )
2, cultural beliefs (ባህላዊ እምነቶቻቺን )
3, quick service (በቶሎ የሚሰጥ አገልግሎት መሆኑ )
4, cheaper fee (ርካሽ መሆኑ )
5, pressure from friends and families (ከጉአደኛ እና ቤተሰብ ከሚመጣ ተፅዕኖ
6, lack of awareness ( የግንዛቤ እጥረት )
ምን ያህል ሰዎች ወጌሻን እንደ መጀመሪያ የህክምና አማራጭ ይወስዳሉ?
በአሁኑ ሰዓት ዘመናዊው የ አጥንት ሕክምና በሃገራቺን እጅግ የተስፋፋ ቢሆንም በየቀኑ ከሚከሰቱ የአጥንት ስብራቶች እና የመገጣጠሚያ ውልቃቶች 85% በመጀመሪያ ወደ ወጌሻ አገልግሎት እንደሚሄዱ በ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተደረገ ጥናት ተረጋግጦአል::
ከነዚህም መካከል 48% ከተወሰኑ ቀናት በሁአላ ወደ ሆስፒታል ምሄዱ ሲሆን 30% የሚሆኑቱ ቀላል እና ከባድ የሚባል ከወጌሻ ጋር የተገናኘ የአካል ጉዳቶች ይከሰትባቸዋል
በወጌሻ ምክንያት ሚከሰቱ የ አካል ጉዳቶች ምንድናቸው?
1, Deformed extremities (መንሻፈፍ )
2, shortening (የእጅ እና እግር ማጠር )
3, joint stiffness (የመገጣጠሚያ መድረቅ )
4, compartment syndrome (በከፍተኛ የጡንቻ ውጥረት የሚከሰት የደም ዝውውር መቁአረጥ )
5, gangrene (የአጥንት እንዲሁም የጡንቻ መበስበስና መሞት )
6, Amputation (የአካል መቆረጥ )
7, septicemia (በደም ውስጥ የተሰራጨ ከባድ የሆነ እንፌክሺን )
8, death following septic shock (በከባድ እንፌክሽን ምክንያት ሚከሰት ሞት)
በአሁኑ ሰዓት ይህንን ችግር ለመቅረፍ ምን እየተደረገ ይገኛል?
1, ለማህበረሰቡ በቂ የግንዛቤ መፍጠር ስራ
2, WHO ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወጌሻ ሚሰሩ አካላት ከ ሕክምና ተቁአማት ጋር ቅርርብ እንዲኖር በማድረግ በቂ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ
3, የአጥንት ሕክምናና በአጥንት ሕክምና የሰለጠኑ ባለሙያዎች በሁሉም አከባቢ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ
ስለዚህ ከኛ ምን ይጠበቃል?
ማንኛዉም የ ስብራትም ሆነ የውልቃት ጉዳት ተከስቶ ይሆናል ብለን ስናስብ ታማሚውን በአስቸኩአይና በቀጥታ ወደ ሕክምና ተቁአማት በማምጣት በቂ ምርመራና ሕክምና እንዲያገኙ በማስቻል የዜግነት ኃላፊነታችንን እንወጣ ::
Telegram: t.me/