21/10/2025
ቀደም ሲል ስንሰጥ ከነበረዉ አገልግሎት በተጨማሪ በቅርቡ አዲስ ባስመጣናቸው የልብ መመርመርያ መሳርያ (ECG) እና የሆርሞን መመርመርያ መሳርያ (Hormone Analyser) በውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት (Internist) ሐኪም ዘወትር ማክሰኞ እና አርብ አገልግሎት መስጠት መጀመራችን ይታወሳል።
አሁን ደግሞ የFNAC እና Peripheral morphology ምርመራ ዘወትር ቅዳሜ ከሚዛን በሚመጡ የስነ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም (Pathologist) አማካኝነት ከደም እና ከሰውነት እባጭ ላይ በሚወሰድ ናሙና ከሳንባ ውጭ የሚገኝ ቲቢ (Extrapulmonary TB)፣ የእንቅርት ህመም፣ የደም ካንሰር እንዲሁም የሌሎች ህመሞችን ምርመራ ጀምረናል።
ቀጠሮ ለማስያዝ በ0970710976 ይደውሉልን።