APHI Woldia Branch /በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ /

  • Home
  • Ethiopia
  • Woldia
  • APHI Woldia Branch /በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ /
Directions Website

APHI Woldia Branch /በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ / Amhara Public Health Institute Woldia Branch (APHI-WB)
በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልድያ ቅርንጫፍ- ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሰሜን ወሎ፣ ለዋግኸምራና ወልድያ ከተማ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል።

ክፍት_የሥራ _ማስታወቂያ_APHI Woldia Branch
12/10/2026

ክፍት_የሥራ _ማስታወቂያ_APHI Woldia Branch

11/10/2026
07/10/2026
23/09/2026

የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እሴቶች 💎

1️⃣በሙያ ብቃት እንክበር
ያለ ክንፍ መብረር፣ ያለ ሙያ መክበር አይቻልምና — በሙያ ብቃት እንክበር!

2️⃣አገልጋይነት ምርጫችን ነው
መታዘዝ ከመስዋዕትነት ይበልጣልና — ምርጫችን አገልጋይነት ነው!

3️⃣በራሳችን ባህል እንደምቃለን
የሰው ወርቅ አያደምቅምና — በራሳችን ባህል እንደምቃለን፣ እንጠብቃለን!

4️⃣ለህግ እንገዛለን
አበው በህግ አምላክ ብለው እንደተገዙለት — እኛም ለህግ እንገዛለን!

5️⃣ሕዝባዊ ወገንተኝነት አጥብቀናል
ከባህር የወጣ ዓሳ ላለመሆን — ሕዝባዊ ወገንተኝነትን አጥብቀናል!

6️⃣አርበኝነት መለያችን ነው
ከመቃብር በላይ ስም ይቆማልና — አርበኝነት መለያችን ነው!

7️⃣ሀብትን በአግባቡ እንጠቀማለን
ብልህ የዓመቱን፣ ሞኝ የእለቱን ነውና — እንደ ብልሆች ሀብትን በአግባቡ ቆጥበን እንጠቀማለን!

8️⃣ልዕለ ሐሳብ ይገዛናል
መልካም ሃሳብ ወንዝ ያሻግራልና — ልዕለ ሐሳብ ይገዛናል!

9️⃣ትኩረታችን ለግቦቻችን ነው
መድረሻውን ያላወቀ የትም ይገኛልና — ትኩረታችን ለግቦቻችን ይሁን!

🔟ብዝሐነትን ተቀብለናል
ልዩነታችን ውበት ነውና — ብዝሐነት ተቀብለናል!

1️⃣1️⃣ምርምርና ፈጠራ መፍቻችን ነው
ቋጠሮ መፍታት ከውሉ እንዲሉ — ምርምርና ፈጠራን ለችግራችን መፍቻ አድርገናል!

1️⃣2️⃣ቅንጅታዊ አሠራር
ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር ነውና — ቅንጅታዊ አሠራር መርጠናል!

1️⃣3️⃣ግልፅነትና ተጠያቂነት
አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ በመሆኑ — ግልፅነትና ተጠያቂነት!

1️⃣4️⃣ቅድመ ጥንቃቄና ምስጢር መጠበቅ
ቅድመ ጥንቃቄና ምላሽ ሰጭነት እና ምስጢር መጠበቅ — እሴቶቻችን ናቸው!

🏥 የአማራ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ

«ለሕብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ»

#እሴቶቻችን 💎 🏥 #ወልዲያ
Amhara Public Health Institute/APHI/
Ethiopian Public Health Institute

22/09/2026

📌 የአማራ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ 🏥

ዋና ዋና ግቦችና ትኩረት አቅጣጫዎች

🎯 8 ዋና ዋና ግቦች
1️⃣የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር
2️⃣የጤና ላቦራቶሪዎችንና ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር
3️⃣የፕሮጀክትና ፕሮግራም አስተዳደር፣ የሀብት አጠቃቀምና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል
4️⃣የኢንስቲትዩቱን ኢንቨስትመንቶች በመሥራት የማህበረሰቡን ጤና አቅም ማሳደግ
5️⃣የጤና መረጃ ስርዓት ልማትና ትንተና
6️⃣የጤና ፖሊሲ አቅጣጫዎችን ማመንጨት
7️⃣የፕሮጀክትና ፕሮግራም አስተዳደር ማሻሻል
8️⃣የኢንስቲትዩቱን ኢንቨስትመንቶች ማሳደግ

🧭 5 ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች 🧭
1. የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር
2. ተግባራዊ የጤና ምርምር ማካሄድ
3. የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ማቅረብ
4. የላቦራቶሪ አቅምን ማጠናከር
5. የጤና መረጃ ሥርዓትን ማሻሻል

#ዋናግቦች 🎯 #ትኩረትአቅጣጫ 🧭 🏥
Amhara Public Health Institute/APHI/
Ethiopian Public Health Institute

«ለሕብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ» 💚💪

20/09/2026
@የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት/APHI/ ተልዕኮ (Mission) 🎯🛡️ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር፣🔬 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣📜 የጤና ፖሊሲ ምክረ ሀሳ...
20/09/2026

@የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት/APHI/

ተልዕኮ (Mission) 🎯

🛡️ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር፣
🔬 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣
📜 የጤና ፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ማቅረብ፣
🧪 የጤና ላቦራቶሪ አቅም ማጠናከር እና
📊 የጤና መረጃ አስተዳደርና ትንተና በማዕከል ማቋቋም የህብረተሰቡን ጤና ማሻሻል።

ራዕይ (Vision) 🌟

ክልላዊ፡ 🏗️ በ2035 አማራ ክልል ለኢኮኖሚ ልማት ጠንካራ መሠረት የጣለ እና የመካከለኛ ገቢ ኢኮኖሚ ባለቤት መሆን።
ተቋማዊ፡ 🏆 በ2035 በአፍሪካ ምርጥ የሕብረተሰብ ጤና ተቋማት መካከል አንዱ መሆን።

📌 የአማራ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ
«ለሕብረተሰብ ጤና ልማት እንትጋ»

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when APHI Woldia Branch /በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ወልዲያ ቅርንጫፍ / posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share