Ensaro wereda health professionals page

Ensaro wereda health professionals page This page to use shared any healthy data

በጥቁር ዱር  ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በዛሬዉ እለት ማለትም በ04/13/2018 ዓ.ሞ የተቋሙን  የ2 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ  አካሂዷል በግምገማዉ ሂደትም:-     👉,የጤና ጣቢያ ሀላፊ  ...
09/09/2026

በጥቁር ዱር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በዛሬዉ እለት ማለትም በ04/13/2018 ዓ.ሞ የተቋሙን የ2 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል በግምገማዉ ሂደትም:-
👉,የጤና ጣቢያ ሀላፊ
👉,የጤና ጣቢያ የመረጃ ባለሙያ
👉,ሁሉም ባለሙያ ተገኝተዋል::
መድረኩም በጤና ጣቢያው ሀላፊ በአቶ ይልማ ጌታቸው የተመራ ሲሆን በግምገማ ሂደቱም
👉,የክትባት የጤና አገልግሎት
👉,ከ5 ዓመት በታች የህፃናት ጤና አገለግሎት
👉,የእናቶች ጤና አገልግሎት
👉,ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ክትትል እና ቁጥጥር ስራ የእቅድ አፈፃፀም
👉, ሪፎርም /Reform/
👉,Data Quality
👉, eCHIS የእነዚህን ተግባራቶች የ2 ወር አፈፃፀም በጥንካሬ እና በድክመት በዝርዝር ተገምግሟል::
በቀጣይ የመስከረም ወር ላይም የሩብ ዓመቱን አፈፃፀም ወደ ሚፈለገዉ ግብ ለማምጣት በድክመት የተገመገሙትን የጤና አገልግሎት ስራዎች እንደ :-
👉, የእናቶች የጤና አገልግሎት
👉,ተላላፊ እና ተላላፈ ያልሆኑ በሽታዎች ክትትል እና የቁጥጥር ስራ
👉, የሪፎርም ስራዎች
👉,የፊዚካል ፓኬጅ ቆጠራ
👉,የመረጃ ጥራትን ማዘመን ዋነኛ የርብርብ ማእከል እና የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ እና ሌሎችንም ባለፉት 2 ወራት የተሻለ አፈፃፀም ያላቸዉን ተግባራቶች ወደ ኋላ እንዳይመለሱ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የግምገማ ሂደቱ ተጠናቋል ::

በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ በጥቁር ዱር ጤና ጣቢያ የካራንባ ቀበሌ የሴቶች የልማት ህብረትና የጎጥ ጤና መሪዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ...
09/08/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ በጥቁር ዱር ጤና ጣቢያ የካራንባ ቀበሌ የሴቶች የልማት ህብረትና የጎጥ ጤና መሪዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ኦሬንቴንሽንና የእናቶች ኮንፈረንስ ተካሄደ። በጥቁር ዱር ጤና ጣቢያ በሚገኘው በካራንባ ቀበሌ ነሀሴ -03/12/2018 ዓ.ም በቀበሌው የሚገኙ ነፍሰጡር እናቶች በተገኙበት የእናቶች ኮንፈረንስ በድምቀት ተካሂዷል።

​ኮንፈረንሱን የመሩት የጥቁር ዱር ጤና ጣቢያ አዋላጅ አቶ ሄኖክ ታምሩ ሲሆኑ፣ በዕለቱ በዋና ዋና የወቅቱ የጤና እና የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

​የስብሰባው ዋና ዋና አጀንዳዎች፡
የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራና
ስለማህፀን መውጣት ምርመራ
​የነፍሰጡር እናቶች ኮንፈረንስ፡ እናቶች በእርግዝና ወቅት ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፣ የዘወትር የጤና ክትትል እና በጤና ተቋም የመውለድ አስፈላጊነት ላይ ገለጻ ተደርጓል።

​የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ፡ የልደት እና ሌሎች የሲቪል ኩነቶች ምዝገባ ለህፃናት መብትና ለሀገር አቀፍ መረጃ ያለውን ከፍተኛ ጠቀሜታ በተመለከተ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

​የክረምት ወቅት የጤና ችግሮች፡ የክረምቱን ወራት ተከትለው የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችንና የጤና ስጋቶችን ለመከላከል መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ውይይት ተካሂዷል።

​አጠቃላይ የጤና ትምህርት፡ በሁሉም የጤና አገልግሎት ተግባራት፣ በግልና አካባቢ ንፅህና አጠባበቅ እንዲሁም በስነ-ምግብ ዙሪያ ሰፊ የጤና ትምህርት ለእናቶች ተሰጥቷል።

​በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ በቀበሌው የሚገኙት የጤና ኤክስቴንሽንና የጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ወ/ሪት አድስ ገለታው እና አቶ አብርሃም አይደፈር ማጠቃለያ ሀሳብ እና መልእክት አስተላልፈዋል። ባለሙያዎቹ እናቶች በስብሰባው ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የራሳቸውን እና የፅንሳቸውን ጤና በጥሩ ሁኔታ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

29/07/2026
28/07/2026
"እንኳን ደስ አላችሁ"በክልሉ ካሉ  ጤና ጣቢያ ውስጥ በመወዳደር ከፍተኛ አፈፃፀም በማምጣት ለሚ ጤና ጣቢያ የምስክር ወረቀትና የሚዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ከጤና ኬላዎች ደግም ደንቢ ጤና ኬላ በተ...
28/07/2026

"እንኳን ደስ አላችሁ"
በክልሉ ካሉ ጤና ጣቢያ ውስጥ በመወዳደር ከፍተኛ አፈፃፀም በማምጣት ለሚ ጤና ጣቢያ የምስክር ወረቀትና የሚዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ከጤና ኬላዎች ደግም ደንቢ ጤና ኬላ በተመሳሳይ ከፍተኛ አፈፃፀም በማምጣት የሰርተፍኬት እና የሚዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
ይህ ውጤት እንዲመጣ ከላይ እስከታች ያደረጋችሁት ተሳትፎ ከፋ ያለ ምስጋና ልናቀርብላችሁ እንወዳለን::
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ።

እንኳን ለ2018 ዓ/ም  ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን ❤❤በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣የጤና  እንድሆንላችሁ እመኛለሁ🙏መል...
11/04/2026

እንኳን ለ2018 ዓ/ም ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን ❤❤በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣የጤና እንድሆንላችሁ እመኛለሁ
🙏መልካም የትንሳኤ በአል ይሁንላችሁ።
Happy Easter ❣️❣️❣️❣️

እንሳሮ ጤና ፅ/ቤት ከወረዳው ካሉት 26 ሴክተር መስሪያቤት በአብይትና ቁልፍ ተግባራት በመወዳደር የ6ወር አፈፃፀም አንደኛ በመውጣት የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል
18/02/2026

እንሳሮ ጤና ፅ/ቤት ከወረዳው ካሉት 26 ሴክተር መስሪያቤት በአብይትና ቁልፍ ተግባራት በመወዳደር የ6ወር አፈፃፀም አንደኛ በመውጣት የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል

የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን በማስመልከት ከእንሳሮ ወረዳ  ጤና  ፅህፈት ቤት ሃላፊና  የእንሳሮ ወረዳ ምክትል  አስተዳዳሪ አቶ  ውብሸት ሙልዬ  የተላለፈ የእንኳ...
06/01/2026

የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን በማስመልከት ከእንሳሮ ወረዳ ጤና ፅህፈት ቤት ሃላፊና የእንሳሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት ሙልዬ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ !!
በወረዳችን ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
የጌታችንና የመድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በእየ አመቱ ታህሳስ 29 ቀን በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡
በዓሉ በቤተ ዕምነቱ እና በምዕመናኑ ዘንድ እጅግ ልዩ ትርጉም ያለው በብዙ ሀይማኖታዊ ስርዓቶች የሚከበር በዓል ነው፡፡
ስለሆነም መላው የዕምነቱ ተከታዮች እና ኢትዮጵያዊን ብዙ ትርጉም ባለው በዚህ በአል እንደከዚህ ቀደሙ በመቻቻል ፣ በመፈቃቀር እና በአንድነት እንድናከብር እያልኩ በወረዳችን ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን ፡-
የእንሳሮ ወረዳ ጤና ፅህፈት ቤት ሃላፊና የእንሳሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዉብሸት ሙልዬ
ታህሳስ 2018 ዓ/ም

25/12/2025
በእንሳሮ ወረዳ  ማህበረሰብ አቀፍ የትራኮማ መድሀኒት እደላ ለሴቶች ልማት ህብረት  ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።
22/12/2025

በእንሳሮ ወረዳ ማህበረሰብ አቀፍ የትራኮማ መድሀኒት እደላ ለሴቶች ልማት ህብረት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

Osoite

Ensaro Health Professional
Lemi
2429

Puhelin

0913242991

Nettisivu

Hälytykset

Tiedä ensimmäisenä ja anna meille oikeus lähettää sinulle sähköpostitse uutisia ja promootioita Ensaro wereda health professionals page :ltä. Sähköpostiosoitettasi ei käytetä muihin tarkoituksiin, ja voit perua milloin tahansa.

Oikopolut

Jaa

Kategoria