Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association

Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association Nonprofit organization inspired by Faith, Hope and LOVE to provide a compassionate care for humanity

ለበጎ አድራጎት የሕክምና አገልግሎት ጥሪበቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እየተሰጠ በሚገኘው ነጻ የሕክምና አገልግሎት ከዚህ በታች የሚገኙ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ...
07/26/2026

ለበጎ አድራጎት የሕክምና አገልግሎት ጥሪ

በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እየተሰጠ በሚገኘው ነጻ የሕክምና አገልግሎት ከዚህ በታች የሚገኙ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ፦
1. Internal Medicine (including residents)
2. Ophthalmology (including residents)
3. Optometry
4. Radiology (including residents)
5. General Surgery (including residents)
6. General Practitioners
7. Other specialists that can offer free services.

አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቀን ከሰኞ - ዓርብ (Monday to Friday)
🕐 ሰዓት
➪ ከ ጧቱ 2:00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት (Time 8፡00 AM -2:00 PM)

ጥያቄ ካለዎት 0931845274 ይደውሉ።

በዚህ አገልግሎት መሳተፍ የምትፈልጉ የጤና ባለሙያዎች ቅጹን በመሙላት አወንታዎቻችሁን እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም!

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 1 ሳምንት ለሚያከናውነው ነፃ የክረምት የጤና ምርመራ ፣ የምክር እና የሕክምና አገልግሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክም.....

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 1 ሳምንት ለሚያከናውነው ነፃ የክረምት የጤና ምርመራ ፣ የምክር እና የሕክምና አገልግሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕ...
07/22/2026

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 1 ሳምንት ለሚያከናውነው ነፃ የክረምት የጤና ምርመራ ፣ የምክር እና የሕክምና አገልግሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር እገዛ ስለሚያደርግ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች በዚህ የበጎ አድራጎት አገልግሎት እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ቀን
➪ ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ
🕐 ሰዓት
➪ ከጠዋት 3:00 ሰዓት - ቀን 10:00 ሰዓት

ቦታ፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል
ጥያቄ ካለዎት 0931845274 ይደውሉ።

በዚህ አገልግሎት መሳተፍ የምትፈልጉ የጤና ባለሙያዎች ቅጹን በመሙላት አወንታዎቻችሁን እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም!

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ከሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ 1 ሳምንት ለሚያከናውነው ነፃ የክረምት የጤና ምርመራ ፣ የምክር እና የሕክምና አገልግሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክም.....

🎉 Congratulations to Dr. Betanas Tafesse and Dr. Yohannes Chemere! 🎉We are thrilled to celebrate the outstanding achieve...
07/02/2026

🎉 Congratulations to Dr. Betanas Tafesse and Dr. Yohannes Chemere! 🎉

We are thrilled to celebrate the outstanding achievement of Dr. Betanas Tafesse and Dr. Yohannes Chemere, esteemed members of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association (EOTMA).

Both physicians successfully matched into Internal Medicine residency programs in the United States during the 2026 Match Season and officially began their residency training on July 1, 2026.

🎓 Dr. Betanas Tafesse began her Internal Medicine Residency at Morehouse School of Medicine in Atlanta, Georgia.

🎓 Dr. Yohannes Chemere began his Internal Medicine Residency at MedStar Georgetown University Hospital in Baltimore, Maryland.

This remarkable milestone reflects their dedication, resilience, and unwavering commitment to excellence in medicine. Their achievements are a testament to years of hard work and perseverance, and we are confident they will make a meaningful impact on the patients and communities they serve.

At EOTMA, we are proud to support physicians pursuing advanced medical training in the United States through mentorship, guidance for ECFMG certification, assistance with the ERAS residency application process, and ongoing professional development.

We also invite aspiring medical students and healthcare professionals to join our EOTMA Student Chapter, where they can benefit from mentorship, volunteer opportunities, networking, leadership development, and valuable academic and clinical experiences.

Please join us in congratulating Dr. Betanas Tafesse and Dr. Yohannes Chemere as they begin this exciting new chapter in their medical careers. We pray that God will continue to bless and guide them as they serve their patients with compassion, excellence, and integrity.

Congratulations! We wish you both continued success and God's abundant blessings!

📣"ሕያውን ከሙታን ጋር ለምን ትሹታላችሁ? በዚህ የለም ፤ ተነስቷል። " ሉቃስ 24 : 5⛪️ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤⛪️አሰሮ ለሰይጣን - አግዐዞ ለአዳም፤⛪️ሰላም...
04/11/2026

📣"ሕያውን ከሙታን ጋር ለምን ትሹታላችሁ? በዚህ የለም ፤ ተነስቷል። " ሉቃስ 24 : 5
⛪️ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
⛪️አሰሮ ለሰይጣን - አግዐዞ ለአዳም፤
⛪️ሰላም - እምይዕዜሰ፤
⛪️ኮነ - ፍስሐ ወሰላም
+ + +
⛪️ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተነሣ፤
⛪️ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤
⛪️ሰላም ከዛሬ ጀምሮ
⛪️ፍጹም ደስታና ሰላምና ሆነ!
⛪️እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን!!!

ሚያዚያ 4 2018
+ + +
⛪️Christ is risen from the dead! - By the highest power and authority!
⛪️He chained Satan! - Freed Adam!
⛪️Peace! Henceforth!
⛪️Is! Joy and Peace

Happy Resurrection Day!!!
April 12, 2026

ከ 6.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ4ኛው ዓመታዊው "መጻጉዕን በመቄዶንያ" ነጻ የሕክምና አገልግሎት ተጠናቀቀ።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር በየዓመ...
03/17/2026

ከ 6.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ
4ኛው ዓመታዊው "መጻጉዕን በመቄዶንያ" ነጻ የሕክምና አገልግሎት ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር በየዓመቱ የሚያደርገውን "መጻጉዕን በመቄዶንያ" ነጻ የሕክምና አገልግሎት ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 6 ለተከታታይ 8 ቀናት ሲያካሂድ ቆይቶ በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ቻለ።
በዚህ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎት ከተሟላ ላቦራቶሪ እና ዲያግኖስቲክ ምርመራ ጋር ለመስጠት ተችሏል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ክፍል ጋርም በመተባበር ለ 293 ሰዎች የዓይን ሕክምና የተሰጠ ሲሆን 54 የዓይን ሞራ ግርዶሽ (Cataract) ተጠቂ የሆኑ ታካሚዎች ተለይተው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተዋል።

በጥርስ ሕክምና ባለሙያዎችም የተሟላ የጥርስ ሕክምና እንዲሁም የጥርስ ነቀላ (Dental extraction) ለማድረግ ተችሏል።

የልብ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎችም በልብ ሐኪሞች የተሟላ ሕክምና የተሰጣቸው ሲሆን 30 ታካሚዎች የልብ አልትራሳውንድ (Echocardiograph) እና ECG ተሰርቶላቸዋል።

በ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪ (ICL) ለ 1000 ታካሚዎች እንዲሁም በ አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ ደግሞ ለ 150 ታካሚዎች የተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ ለማድረግ ተችሏል።
በተጨማሪም የፊዚዮቴራፒ እና የደረቅ መርፌ (Acupuncture) ሕክምና በባለሙያዎች የተሰጣቸውም ይገኙበታል።

በዚህ አገልግሎት ከተለያዩ የሕክምና ስፔሺያሊቲ እና የጤና ሙያ የተውጣጡ ከ160 በላይ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 50 ስፔሺያሊስት፣ 6 ሰብስፔሺያሊስት ሐኪሞች ፣ 44 ጠቅላላ ሐኪሞች፣ 30 ነርሶች፣ 8 የጥርስ ሐኪሞች፣ ፋርማሲስቶች፣ ፊዚዮቴራፒስቶች፣ የስነእምሮ እና የማኀበረሰብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የላቦራቶሪ ቴክኒሺያኖች ይገኙበታል።

በ4ኛው ዓመታዊው "መጻጉዕን በመቄዶንያ" ነጻ የሕክምና አገልግሎት ባጠቃላይ 1070 ታካሚዎች የተለያዩ የሕክምና አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሲሆኑ አጠቃላይ የተሰጠው የሕክምና አገልግሎትም በገንዘብ 6,502,115 ብር የሚገመት ነበር።
ለዚህ አገልግሎት መሳካት የረዳችሁንን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ክፍል ፣ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪ (International clinical laboratories)፣ አርሾ ሜዲካል ላቦራቶሪ (Arsho medical labratories P.L.C) ፣ ያኔት አጠቃላይ ሆስፒታል (Yanet General Hospital)፣ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል (Zewditu Memorial Hospital)፣ ኦቶሪኖ ልዩ የአንገት በላይ ክሊኒክ (Otorino Ent Surgical Center) ፣ Badreg Pharmaceuticals እና ELPIS PHARMACEUTICALS በአገልግሎቱ ተጠቃሚ በሆኑት ወገኖቻችን ስም ለማመስገን እንወዳለን። ለጤና ባለሙያዎችም የምግብ አቅርቦት ድጋፍ ላደርጉልን ROMi Catering & Restaurant ከልብ እናመሰግናለን።

በዚህ የበጎ ፈቃድ የሕክምና አገልግሎት ለሳተፉት ባለሙያዎች እና ለአገልግሎቱ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶች የምስጋና ምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን፤ ጊዜያችሁን እና ሙያችሁን በነጻ ለወገናችሁ በመለገስ ለሰጣችሁት አገልግሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለማመስገን እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር
“አክብሮትና ትህትናን የተላበሰ የጤና አገልግሎት ለሰው ልጆች በሙሉ”

Congratulations to Our Newly Matched Physicians!Today we proudly celebrate members of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Me...
03/16/2026

Congratulations to Our Newly Matched Physicians!

Today we proudly celebrate members of the
Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association (EOTMA)
who successfully matched into residency programs through the
National Resident Matching Program (N**P) on Match Day — March 16, 2026.

After years of dedication, perseverance, and commitment to the healing profession, these outstanding physicians have reached an important milestone in their medical journey.

Your achievement reflects not only academic excellence but also a deep calling to serve humanity with compassion, integrity, and faith.

As you begin residency training, we pray that God grants you wisdom, strength, and humility as you care for patients and advance the noble mission of medicine.

We are incredibly proud of you and look forward to the impact you will make in healthcare and in our communities.

May God bless your journey ahead.

Congratulations, Doctors!

03/07/2026

ለ “4ኛው ዓመታዊው መጻጉዕን በመቄዶንያ” አገልግሎት የተመዘገባችሁ የሕክምና ባለሙያዎች ለበጎ ፈቃደኝነታችሁ ከወዲሁ እያመሰገንን ፤ አገልግሎቱ የሚጀመረው ነገ ስለሆነ በተመዘገባችሁት ቀን እና ሰዓት በቦታው በመገኘት የአገልግሎቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ አደራ እንላለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር

4ኛው ዓመታዊው መጻጉዕን በመቄዶንያ ነጻ የሕክምና አገልግሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር በየዓመቱ የሚያደርገውን "መጻጉዕን በመቄዶንያ" የተሰኘውን ነጻ የሕክምና አገልግሎት...
02/26/2026

4ኛው ዓመታዊው መጻጉዕን በመቄዶንያ ነጻ የሕክምና አገልግሎት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር በየዓመቱ የሚያደርገውን "መጻጉዕን በመቄዶንያ" የተሰኘውን ነጻ የሕክምና አገልግሎት 4ኛ ዙር ዘንድሮም ከተለያዩ የሕክምና ስፔሺያሊቲ እና የጤና ሙያ በተውጣጡ ባለሙያዎች ከ የካቲት 29 - መጋቢት 6 (March 8 - 15 ) ለ 8 ቀን የሚቆይ አገልግሎት ይሰጣል። በዚህ አገልግሎት ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ባለሙያዎች የምዝገባ ቅጹን በመሙላት አውንታችሁን እንድታሳውቁን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ቀን፡ የካቲት 29 - መጋቢት 6 // Date: March 8 - March 15

ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2፡30 - 11:00 ሰዓት // Time: 8:30 AM - 5:00 PM

ቦታ፡ መቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል

ለዚህ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ባለሙያዎች የሚከተሉት ናቸው፦

Specialties needed are:
General Practitioners
Internal Medicine
Cardiology
Nursing
Dentists
Dermatology
Pharmacists
Ophthalmology
Public Health Experts
ENT
Orthopedics
Urology
Neurology
Neurosurgery
Social Worker
Mental Health
Psychiatry
Health Officers
General Surgery
Laboratory Technicians
Physiotherapists

ጥያቄ ካለዎት በ 0944111990 ይደውሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር

“አክብሮትና ትህትናን የተላበሰ የጤና አገልግሎት ለሰው ልጆች በሙሉ”

https://forms.gle/2ozP8vAh2dfy5sRV6

የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል በጥምቀት በዓል ላይ አገልግሎት ሰጠ።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ...
01/20/2026

የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል በጥምቀት በዓል ላይ አገልግሎት ሰጠ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ እንደሚያደርገው በጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት አገልግሎት ለመስጠት ችሏል።

በዚህም አገልግሎት ከተለያዩ ስፔሺያሊቲ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር በዕለቱ በበጎ አገልግሎት ለተሳተፉ የጤና ባለሙያዎች የላቀ ምስጋና ለማቅረብ ይወዳል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር የአደባባይ በዓላት ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ክፍል የአደባባይ በዓላት ላይ እና ህዝብ በሚበዛባቸው ክስተቶች (Public events) ላይ የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 5 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም አገልግሎት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ብዙዎችም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር ለሁሉም በሁሉም!
# eotma_for_all_by_all

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ...
01/06/2026

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

" ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" ኢሳይያስ 9፡6

Happy Nativity Feast!

"For unto us a child is born, unto us a son is given: and the government shall be upon his shoulder: and his name shall be called Wonderful, Counsellor, The mighty God, The everlasting Father, The Prince of Peace." Isaiah 9:6

Address

1511 Bankbury Way
Chesapeake, VA
23322

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Orthodox Tewahedo Medical Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share