27/08/2026
ከጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ቀዶ ሕክምና በኋላ መንበርከክ ይቻላል?
አጭሩ መልስ አዎ፣ ይቻላል! ነገር ግን የመንበርከክ አቅም እና ምቾት ከሰው ሰው ይለያያል።
1. መንበርከክ ለምን ሊከብድ ይችላል?
🔹በቁስሉ ዙሪያ የሚኖር መደንዘዝ ወይም ሕመም
🔹የመገጣጠሚያ መወጠር (Stiffness) እና የጡንቻ ጥንካሬ እና አቅም ማነስ
🔹መገጣጠሚያው ይጎዳል የሚል ፍርሃት
2. መንበርከክ መቼ መጀመር አለበት?
ለሁሉም ታካሚዎች አንድ የተወሰነ ሳምንት የለውም። ነገር ግን ከመጀመርዎ በፊት፦
🔹የቀዶ ሕክምና ቁስሉ ሙሉ በሙሉ የዳነ መሆን አለበት።
🔹እብጠቱ ጠፍቶ እና ከስሞ የመታጠፍ አቅም እና የጡንቻ ጥንካሬ መመለስ አለበት።
3. ደረጃ በደረጃ የሚደረግ የመለማመጃ መንገድ፦
በቀጥታ ጠንካራ ወለል ላይ ከመንበርከክ ይልቅ ቀስ በቀስ መለማመድ ያስፈልጋል፦
🔹መቆም ➔ ድጋፍ ይዞ መንበርከክ ➔ ለስላሳ ፍራሽ/ሶፋ ➔ ውፍራም ትራስ ➔ ስስ ትራስ ➔ ምንጣፍ ➔ መደበኛ ወለል
መንበርከክ አለመቻል የቀዶ ሕክምናው አልተሳካም ማለት አይደለም። የሕክምናው ዋና ዓላማ ወደ ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ እና ነፃነትዎ እንዲመለሱ መርዳት ነው።
ቀጠሮ ለመያዝ፦
ስልክ፦ +251 933 91 92 99
- -
Can You Kneel After a Total Knee Replacement?
The short answer is yes, many patients can! However, the ability to kneel comfortably varies from person to person.
1. Why Can Kneeling Feel Difficult?
🔹Numbness or sensitivity around the incision site.
🔹Joint stiffness or reduced flexibility.
🔹Fear that kneeling will damage the implant (Proper kneeling does not harm your knee replacement).
2. When Can You Start?
There is no fixed timeline. Before trying to kneel.
🔹The surgical incision must be completely healed.
🔹Swelling should be resolved.
🔹Knee flexion, strength, and control must be adequate.
3. The Step by Step Approach
Do not kneel directly on hard floors right away. Progress gradually:
🔹Standing → Supported Kneeling → Soft Cushion → Folded Towel → Carpet → Regular Floor
The Key Takeaway:
Difficulty kneeling does not mean your surgery failed. The ultimate goal of a knee replacement is returning to your daily activities and regaining your independence.
Contact & Appointments:
Phone: +251 933 91 92 99
#ጉልበት #መገጣጠሚያ